Weight | 34 g |
---|
ደስ የሚል ጉዞ
$4.00
የተለያዩ የአፃፃፍ ስልቶችን በመከተል በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የእስልምናን ትምህርት ጭብጥ ለሙስሊሙም ሆነ ለሌላው ማህበረሰብ ማድረስ አስፈላጊ ነው፡፡ ከስልቶቹም መካከል ብዙዎቹን አልተጠቀምንባቸውም፡፡ የትረካና የወግ የአፃፃፍ ስልት የንባብ ባህላችንን ይበልጥ ለማዳበርንና አንድን ቁምነገር አዝናኝና ሳቢ በሆነ መልኩ ለማስተላለፍ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍም በዚያ መልኩ የተዘጋጀ ነው፡፡መጽሐፉ የእስልምናን መልዕክት አዝናኝና አስተማሪ በሆነ መልኩ ለማስተላለፍ የተሞከረበት ነው፡፡
አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ሰዒድ
የገጽ ብዛት ፡ 56
የታተመበት ዓመት ፡ 2007
ከመጽሐፉ ፡
ድንገት ራሴን ጠየቅኩኝ፡፡ በሷ ላይ ዐይኔ እያየ የደረሰው ሞት በኔ ላይ ቢደርስ ኖሮ ምን ይውጠኝ ነበር? ምን ይሆን ዕጣ ፈንታዬ? እጅግ ከመደናገጤና ከመፍራቴ የተነሳ መልሱን ፍለጋ ጊዜ አላጠፋሁም፡፡ ትኩስ እንባ እንደ ጅረት ፈሰሰኝ… ተቃጠልኩ… ፀፀቴ እጅጉን በዛ፡፡
አላሁ አክበር! አላሁ አክበር! … ለሱብሒ ሰላት አዛን እየተደረገ ነበር፡፡ ሌላ ጊዜ በፊልም ዛሬ ደግሞ በእህቴ ሀሳብ ላይ ሆኜ ሌሊቱ ነጋ፡፡ ዛሬ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ አዛኑን ከልብ ሆኜ አዳመጥኩት፡፡ ዋ.. እንዴት ይጣፍጣል በአላህ!! እንዴትስ ይጥማል!! በርጋታ አጣጣምኩት፡፡
ሙአዚኑ የሚለውን ደጋግሜ አልኩኝ፡፡ አዛን ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ የሰማሁ ያህል አዲስ ሆነብኝ፡፡ የሰላት ልብሴን አነሳሁና ፈጅር ለመስገድ ተነሳሁ፡፡ እህቴ እንደሰገደችው ሁሉ እኔም የመጨረሻ መሰናበቻ ሰላቴን ሰገድኩኝ፡፡ የሱብሒ ሰላት በዚህች ዓለም ላይ የመጨረሻ ሰላቷ ነበር፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት