ይህ ነው ኢስላም

$5.00

ስለ ኢስላም ማወቅ ለሚፈልጉ ሁሉ ግን ኢስላም ምንድነው? ስለ እምነት ማብራሪያ፣ የኢማን ሚስጢሮች፣ የአላህ (ሱ.ወ.) አንድነት፣ አላህን መውደደድና መፍራት፣ የዒባዳ መገለጫዎች፣ የዒባዳ የመጨረሻ ግብ፣ የአላህ (ሱ.ወ.) ባህሪያት በቁርኣን፣ የአላህ ጌትነት መሰረቶች፣ የኢማን ፍሬ፣ ለአላህ ፈቃድ እጅ መስጠት፣ የኢማን መዕዘናት ትንታኔ እኔ ሌሎችም ውብ በሆነ መልኩ የተዳሰሱበት፡፡ አዘጋጁ የረጅም ዘመን አስተውሎታቸውን የምርምር ሥራቸውን ነው ወደ መጽሐፍ የለወጡት፡፡ የመምህርነት ዘመን ልምዳቸውን፣ የሥራ ሕይወታቸውንና ገጠመኛቸውን ለዚህ መጽሐፍ ግብአት አውለውታል፡፡ መጸሐፉ የሐሳብ አወቃቀሩ የቋንቋ አሰዳደሩ የተምሳሌት አጠቃቀሙ፣ የምናብ ምጥቀቱ፣ ተወዳጅ እንዲሆን አድርጐታል፡፡
ዝግጅት ፡ ሸይኽ ዐሊ ጠንጣዊ
ትርጉም ፡ ሑሴን ባድሼ
የገጽ ብዛት ፡ 187
የታተመበት ዓመት ፡ 2004
አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት
ከመጽሐፉ በጥቂቱ …
በአንድ ወቅት ለተማሪዎቼ የሆነ እንግዳ መጥቶ ‹ስለ ኢስላም በአንድ ሰዓት ውስጥ አብራሩልኝ፡፡› ብላችሁ ምን ትላለችሁ አልኳቸው፡፡ ተማሪዎቼም ‹በአንድ ሰዓት ውስጥ? አይሆንም እንጂ ይህን ለመግለጽ ተውሒድ መማር አለበት፣ ተፍሲር መማር አለበት፤ ሐዲሥን ማወቅ ሸሪዓንም መረዳት ይኖርበታል፡፡› አሉኝ፡፡ ይሄን ሁሉ በአንድ ሰዓት ውስጥ ኦ .. አይታሰብም እንጂ፡፡ ይህን ለመግለጽ ቢያንስ አንድ ሃምሳ አመት ሳያስፈልገው አይቀርም፡፡› አሉኝ፡፡ (በርግጥ ነገሩ እነሱ እንዳሉት ነውን? ) …. የምር ግን ኢስላም ምንድነው? …
ኢስላም የራሱ የሆኑ መርሆች አሉት፡፡ …..
ይህ ቁሳዊ ዓለም የሁሉ ነገር መጀመሪያና መጨረሻ አይደለም፡፡ ከዘላለማዊዉ ህይወት ትንሹና አንዱ ክፍል ብቻ ነው፡፡
የሰው ልጅ ከመወለዱ በፊትም ነበር፡፡ ከሞተም በኋላ በህይወት ይቀጥላል፡፡ ሰው ራሱን ከማወቁም ቀደም ብሎ ተፈጠረ እንጂ ራሱን አልፈጠረም፡፡
በሰው ዙሪያ ያሉ ቁሳቁሶች ፈጣሪ አይደሉም፡፡
በፍጥረተዓለሙ ውስጥ ያሉ ነገሮች በአላህ ችሎታ ካለመኖር ደመኖር የመጡ ናቸው፡፡
ፈጣሪም ገዳይም ኣህ (ሱ.ወ.) ብቻ ነው፡፡ የሁሉ ነገር ፈጣ የሆነው አላህ ከፈለገም ሁሉንም ያጠፋቸዋል፡፡
አላህ (ሱ..ወ.) ከፍጡራኑ መካከል ማንንም አይመስልም፡፡ ቀድሞም የነበረ ወደፊትም የሚኖር ዘላለማዊ አምላክ ነው፡፡
አላህ (ሱ.ወ.) በሰው ቋንቋ ከሚገለፀው በላይ ፍፁም ፍትሃዊ ነው፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: