Weight | 176 g |
---|
የፍልስጤም የነፃነትና የፍትህ ጥያቄ
$4.00
ከዛሬ ሰባ ምናምን ዓመት በፊት ፍልስጤም ነፃ አገር ነበረች፡፡ ኋላ ላይ በአንዳንድ ኃያላን አገር ይሁንታና አስተባባሪነት አይሁዳውያን ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተጠራርተው በጥገኝነት በፍልስጤም ምድር ሰፈሩ፡፡ በነርሱ እየታገዙና እየተስፋፉ በዚያው ምድር ኢስራኤል የምትባል አገር መሠረቱ፡፡ ቀስ በቀስም ጥንታዉያኑን ነባር ሕዝቦች ፍልስጤማዉያንን ክግዛታቸው ማፈናቀልና ከገዛ አገራቸው ማባረር ጀመሩ፡፡ አሁን ላይ ፍልስጤማውያኑ በገዛ አገራቸው ባይተዋር ሆነዋል፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት ደግሞ ስደተኞች ሆነዋል፡፡ ግና ችግራቸው ዉስብስብ ቢሆንም ትግላቸዉን አላቆሙም፡፡ ይህ መጽሐፍ ይህንኑ ጉዳዩ ሚዛናዊና መሳጭ በሆነ መልኩ ይዳስሳል፡፡
አዘጋጅ ፡ ስለሺ ቱጂ
የገጽ ብዛት ፡ 188
የታተመበት ዓመት ፡ 1997
ከመጽሐፉ ፡
አገሩ የኛ ነው፤ ከጥንት ጀምሮ የኛ ነበር፡፡ ከነርሱ ይልቅ እኛ በአገሩ ዉስጥ ለረጅም ጊዜ ኖረናል፡፡ ከነርሱ በተሻለም አገሩ ላይ ሠርተናል ደክመናል፡፡ እኛ ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ከምድሩ ጋር ያለን ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ግንኙነት ከአይሁዶች በእጅጉ ይልቃል፡፡ ስለዚህ እነርሱ ምድሩ ላይ አለን የሚሉት ጥንታዊ ታሪካዊ መብት አገሩን የመውሰድ መብት አይሠጣቸዉም፡፡ በተመሣሣይ መልኩ እኛም ዐረቦች በጥንታዊ ቤታችን ስፔን ላይ ያለንን ታሪካዊ መብት መጠየቅ አንችልም፡፡ ስፔን በዐረቦች ለስምንት ምዕተ ዓመታት በተዳደችበት ወቅት ገናና ከመሆኗም በተጨማሪ ለዘመናዊ የአውሮፓ ሥልጣኔ ፈርቀዳጅ ሆናለች፡፡ ….
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት