የዱዓ ምንነቱና ትሩፋቱ

3.00 $

ይህ መጽሐፍ ለችግሮቻችን ሁሉ መፍትሔ ስለሚሠጠን ጉዳይ አመላካች መረጃን የሚሰጠን ነው፡፡ ይኸውም ሲባል ዱዓ፡፡ ዱዓ በየትኛውም የሰው ልጅ የስሜት ሁኔታ ማለትም በሐዘንም ሆነ በደስታ በችግርም ሆነ በድሎት በጭንቀትም ሆነ በፍስሐ ወቅት አስፈላጊ ትጥቅ ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ዉስጥ በማራኪ የአገላለጽ ሥልት የታላላቅ ዑለማዎችን የዱዓ እሳቤ እናነባለን፡፡ ሰው እንዲወድህ ከፈለግህ አትለምነው አላህ እንዲወድህ ከፈለግክ ግን ለምነው፣ ተለማመጠው የሚለውን አባባል መጽሐፉ ያስታውሰናል፡፡ ከዚህ በተቃራኒውም ብናስብ አላህ እንዲጠላን ከፈለግን አላህን አለመለመን ብቻ ይበቃናል፡፡ በዚህ መጽሐፍ ብዙ ቁምነገሮችን እንጨብጣለን፡፡
መጽሐፉ በዋናነት ስለ ዱዓ ምንነትና አስፈላጊነት ይዘረዝራል፡፡ ዱዓእ ስላለው ትሩፋትም ይተነትናል፡፡
አዘጋጅ ፡ ሸይኽ ኢብራሒም ሐቂ
ትርጉም ፡ ዐብዱልባሲጥ ጁነይድ
የገጽ ብዛት ፡ 133
የታተመበት ዓመት ፡ 2005
ከመጽሐፉ ፡ ኢማም አልገዛሊ የዱዓን ጥም ሲያብራሩ “የአላህን ፍርድና ዉሳኔ ተፈፃሚ እንዳይሆን የሚያግደው ምንም ነገር እንደሌለ ይታወቃል፡፡ ታዲያ ዱዓ የማድረግ ጥቅሙ ምን ላይ ነው በማለት ከጠየቅከኝ ምላሼ ከአላህ ፍርድና ዉሳኔዎች መካከል አደጋን በዱዓ መከላከልና ማስወገድ እንደሆነ እወቅ የሚል ነው፡፡ ምክንያቱም ጋሻ ቀስትን ለመመከት እንደሚያገለግለው ሁሉ …..
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ

Additional information

Weight 134 g