Weight | 184 g |
---|
የደጋጎች ፈለግ
$2.00
ኢማናችን ሲደክም በተለያዩ ነገሮች ማከም ግድ ይለናል፡፡ ከነኚህም ማከሚያዎች መካከል አንዱ የቀደምት ደጋግ ሰዎችን መልካምነት፣ የአምልኮ ተግባራት ላይ ያላቸዉን ጥንካሬ፣ ለዚህች ዓለም ያላቸዉን ንቀት፣ መልካም አባባሎቻቸዉን፣ ለአላህ ሱ.ወ. የነበራቸዉን የፍራቻ ጥግ እና በሌሎችም ሊሆን ይችላል፡፡ እነኚህ ሁሉ መለስ ብለን ወደራሣችን እንድንመለከት የሚያደርጉን ነገሮች ናቸው፡፡ ይህች መጽሐፍ የነኚህ ነገሮች ስብስብ ናት፡፡ የተለያዩ አባባሎቻቸዉን፣ ገድሎቻቸዉን፣ ታሪኮቻቸዉን ታወሳለች፡፡ በቀልባችን ላይም የኢማን ቁጭት ስሜት ታጭራለች፡፡
ትርጉም ፡ አሕመድ ሑሴን/አቡ ቢላል
የገጽ ብዛት ፡ 196
የታተመበት ዓመት ፡ 2012
ከመጽሐፉ ፡ ሀምዛ አል-አዕማ እንዲህ ብሏል፦ “ሐሰን አል-በስሪን ልጎበኛቸው (ልዘይራቸው) በሄድኩ ቁጥር ሲያለቅሱ ነው የማገኛቸው። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሶላት ላይ ሆነው ሲያለቅሱ ያጋጥሙኛል። አንድ ዕለት ታዲያ፦ “ ለምን በጣም ያለቅሳሉ?” አልኳቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሉኝ “አይ የምወድህ ልጄ! አማኝ የሆነ ሰው ካላለቀሰ ታዲያ ምንድን ነው የሚያደርገው? ልጄ ሆይ! ለቅሶ የእርሱን (የአላህን) እዝነት ያስገኛል። ቀሪውን ሕይወትህን እያለቀስክ ማሳለፍ ከቻልክ አድርገው። በዚህ ምክኒያት አላህ ያዝንልህ ይሆናል።
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት