የደስታ ጐዳና

2.00 $

የሰው ልጅ በተደጋጋሚ ነፍሱን የሚያሳጡና ምሬት የሞላባቸው ገጠመኞች ሲያስተናግድ ይስተዋላል፡፡ ደስታውን የሚያሳጡት የአስተሳሰቡ ነፀብራቆችና በራሱ እይታዎች ላይ የተገደቡ ሁኔታዎች ናቸው፡፡ ያጋጠሙትን ክስተቶች መታገስ ቢችልና አእምሮውን ለአጋጣሚዎች ዝግጁ ቢያደርግ፣ ከዓለም ሁኔታ ራሱን ባስማማ፡፡ ደስታን ማጣት በዓለማችን የብዙ ሰዎች ችግር ነው፡፡ ይህ አነስተኛ መጽሐፍ ሰዎች እንዴት ደስተኛ የሆነ ሕይወትን መምራት እንደሚችሉ የተለያዩ መረጃዎችን ይሠጣል፡፡ ስለ ደስታ ምንነትና ደስታ ስለሚገኝባቸው መንገዶች ይዳስሳል፡፡
ዝግጅት ፡ ጋሊብ አሕመድ እና ነዚፍ ጃሚዕ
ትርጉም ፡ አሕመድ ሑሴን (አቡ ቢላል)
የገጽ ብዛት ፡ 80
የታተመበት ዓመት : የካቲት 2000
ከመጽሐፉ፡
ደስታና ገንዘብ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ሆነው የሚላቀቁ እስከማይመስሉ ድረስ ብዙ ሰዎች ይነሆልሉባቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ በሀብት ባህር ዉስጥ የሰጠሙ ሰዎች የታላላቅ የንግድ ተቋም ባለቤቶች የሰፋፊ ቦታዎችና ህንፃዎች ባለንብረቶች ቁጥሩ የማይታወቅ ገንዘብ የሚያገላብጡ ሰዎች በርግጥ ብዙ ከሚወሳለት ደስታ ጋር ትዉዉቃቸው እስከምንድረስ ይሆን? ብሎ የሚጠይቅ ብልህ አሳቢ ግን ብዙም አያጋጥምም ለምን? …
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: