Weight | 26 g |
---|
የዝምድና ሐቅ በኢስላም
1.00 $
የዝምድና ሐቅ በኢስላም ትልቅ ቦታ የሚሠጠው አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ዛሬ ላይ ግን ብዙዎች ይህን ጉዳይ ችላ ሲሉት ይታያል፡፡ መጽሐፏ በዚሁ ዙርያ ከቁርኣን አንቀጾች፣ ነቢያዊ ሐዲሦችና የዑለማዎች ንግግሮች በመጥቀስ ታስታውሰናለች፡፡ የዝምድናን ምንነት፣ ዝምድና መቼ እንደሚቀጠልና መቸ እንደሚቋረጥ፣ የዘመዶችንና የዝምድና የመቀጠል ትሩፋቶችን እንዲሁም ዝምድና የመቀጠያና ዝምድና የመቁረጫ ተግባራትንና ሌሎችንም ተያያዠነት ያላቸውን ጉዳዮች ታነሳለች፡፡
አዘጋጅ ፡ ጁነይድ ዐብዱልመናን ዑመር
የገጽ ብዛት ፡ 40
የታተመበት ዓመት ፡ ግንቦት 2011
ከመጽሐፉ ፡ ኢስላም ዝምድናን መቀጠልና ዘመዶችንም መንከባከብን ለመደንገጉ ምክኒያት የሚሆኑ በርካታ ጥበባት (ሚስጥሮች) ያሉ ሲሆን ከዋና ዋናዎቹ መካከል፡ ዘመድን ማስደሰት፣ በአንድ ቤተሰብ መካከል ማህበራዊ መደጋገፍን ለማረጋገጥ፤ የራስን ክብርን ለመጠበቅ፣ በህይወት እያለ በጎ ሲያደርግላቸው የነበረውን ሰው ዘመዶቹ በሚያደርጉለት ዱዓ ከሞት በኋላም ምንዳውን እንዲጨምር ማድረግ ይገኙበታል፡፡ እንደዚሁም ዝምድናን የሚቀጥል ሰው በዚህች ዓለምም የሚያገኘው ጥቅም አለ፡፡ ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል – ‹‹ ሲሳዩ እንዲሰፋና ፋናው እንዲያምር የፈለገ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል፡፡›› (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል፡፡)
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት