የዕውቀት ኃይል በኢስላም ቁ.2

$3.00

መጽሐፍ በቁጥር አንድ እና ሁለት የተዘጋጀ ነው፡፡ በዕውቀት ዙርያ አስፈላጊ የሆኑ ሊታወቁም የሚገቡ በርከት ያሉ በተለያየ ርዕስ ዙርያ የሚያተኩሩ መረጃዎች በተደራጀ መልኩ የታጨቁበት ነው፡፡ ዕውቀት ምን ያህል ኃያል እና አስፈላጊ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ሙስሊሙ ለዕውቀት ያለው አመለካከት ከፍ እንዲል ይወተዉታል፡፡
አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ዑመር አደም
የገጽ ብዛት ፡ ቁጥር አንድ 231 ገፆች
ቁጥር ሁለት 112 ገፆች
የታተመበት ዓመት ፡ 2007
ከመጽሐፉ ፡
እውቀት:- ጥልቀት የማይርቀው እጅ፤ ርቀት የማያደክመው እግር፤ ድምጽ የማይደብቀው ጆሮ፤ አጣርቶ የሚናገር ምላስ፤ አነፍንፎ የሚደርስ አፍንጫ ነው፡፡ እውቀት:- የሚስጥር ሶላት፤ የነፍስያ ማሰልጠኒያ ጾም፤ ደካሞችን ማስጠለሊያ ዘካ፤ ሰዎችን በእውነት ጥላ ስር የሚያሰባስብ ሃጅ ነው፡፡ እውቀት:- ከቤተሰብ የማይወረስ ሃብት፤ ከገበያ የማይሸመት ንብረት፤ በሽልማት የማይሰጥ ወርቅ፤ በጉልበት የማይነጠቅ ምርኮ፤ በህልም የማይታይ ጸጋ፤ በምኞት የማይገኝ ገንዘብ ነው፡፡ እውቀት:- ስጦታ የማይቀንሰው፤ ቦታ የማይጠበው፤ ሌባ የማይሰርቀው፤ ሸክሙ የማይከብድ፤ እድለኞች የሚያገኙት፤ እድለ ቢሶች የማያጡት፤ ህልቆ ስፍር የሌለው ሃብት ነው፡፡

በዉስጣችን ያሉ መረጃዎች በየጊዜው ካልተቃኙ ፈጥነው ያፈተልካሉ፤ በቀላሉ ቀለማቸው ይደበዝዛል፤ ከህሊናም ይሰወራሉ፤ የጊዜ መርዘም ተጽዕኖ የማያሳድርበት ነገር የለም፡፡ ቁርኣን ጭምር በየጊዜው ካላዩትና ከተተው እንደሚጠፋ ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ. ተናግረዋል
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: