የውመል ቂያማ

4.00 $

በኢስላም ዉስጥ ከስድስቱ የእምነት ማዕዘናት መካከል አንዱ በመጨረሻው (የትንሳኤ ቀን ማመን ) ነው፡፡ የፍርዱ ቀን (የውመል ቂያማ) የሰውን ብቻ ሳይሆን የዚህን አጽናፍ ዓለም ሞት (መፈራረስ) የሚያስከትል ቢሆንም በሚያስደንቅ ሁኔታ አብዛኛው የዓለም ሕዝብ ፈጽሞ ሊያስበውና ሊጨነቅበት የማይፈልገው ጉዳይ መሆኑ እውነት ነው ይላል ደራሲው፡፡ ይህ የውመል ቂያማ የተሠኘው መጽሐፍ ስለዚሁ ቀን ዉሎ ቁርኣንን ሳይንስን እያዛመደ ይተነትናል፡፡ የመጨረሻውን የአላህን ፍርድ ቀን አሳዛኝ የዓለም ፍጻሜን ያስቀኘናል ፡፡
ዝግጅት ፡ የሃሩን ያሕያ
ትርጉም ፡ አሕመድ ሑሴን (አቡ ቢላል)
የገጽ ብዛት ፡ 136
የታተመበት ዓመት ፡ ነሐሴ 2002
ከመጽሐፉ ፡ ጊዜ በአክናፎቹ ወደፊት በገሰገሰ ቁጥር የፍርዱን ቀን ወደኛ እያቀረበው መሄዱ የታወቀ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ብዙ ሰዎች ያንን ቀን እጅግ ሩቅ እንደሆነ አድርገው ያስባሉ፡፡ የዚህች ዓለም ዕድሜ አንድ ቀን ፍፃሜ ያገኛል፡፡ የፍፃሜዋን ቀን በትክክል የሚያውቅ ዓለምን የፈጠራት ጌታ አላህ (ሱ.ወ.) ብቻ ነው፡፡ በዚህች ዓለም ላይ የኖረን ለትንሽም ሆነ ለረጅም ጊዜ የቆየ ሰው ሁሉ አላህ ፊት መቅረቡ አይቀርም፡፡ …
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: