Weight | 85 g |
---|
Moral & Social Issues
የወላጅ ሐቅ
3.00 $
ኢስላም ለወላጆች ትልቁን ቦታ አጐናጽፏቸዋል፡፡ አላህ ከራሱ አምልኮ ቀጥሎ የወላጆችን ጉዳይ አደራ ብሏል፡፡ ወላጆችን አስመልክቶ በርካታ የቁርኣን አንቀጾች ቁርኣን ውስጥ እናገኛለን፡፡ ይህም ሆኖ በአሁኑ ዘመን የወላጆች ደረጃ እየተዘነጋ የመጣ ይመስላል፡፡ አንዳንድ ልጆች በወላጆቻቸውና በነሱ መካከል ያለውን ርቀት ከመዘንጋት አልፈው ወላጆቻቸውን የመናቅ የማንኳሰስ ስሜትን እያሳዩ ነው፡፡ በሥነ-ምግባር የተበላሹ ልጆች የመኖራቸውን ያህል ለወላጆቻቸው ቅንና ታዛዥ የሆኑ ልጆችም አሉ፡፡ የመጽሐፉ አዘጋጅ ለወላጆች ቅን ስለመሆን፣ በወላጆች ላይ የማመጽ አደገኛነትና ስለ ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች አውስቷል፡፡
ዝግጅት፡ ዐብዱልመሊክ ቃሲም
ትርጉም ፡ ሑሴን ኸድር
የገጽ ብዛት ፡ 79
የታተመበት ዓመት ፡ መጋቢት 2003
ከመጽሐፉ ፡
“አቡበክር የተባሉት ታላቅ ዓሊም ‘ዛዱል ሙሳፊር’ በተሰኘው መጽሐፋቸው ‘አንዳች ነገር በመሥራቱ ወላጆቹ የተቆጡት ወይም ያለቀሱበት (ሰው) በፍጥነት አንዳች የሚያስደስታቸውን ወይም የሚያስቃቸውን ነገር ማድረግ አለበት።’ ይህ ማለት ወላጆች አንዳች የሚያስፈልጋቸው ነገር ሲያዙ ፈጥኖ በመታዘዝ አክብሮትን ማሳየት ነው። ማንኛውንም ትዕዛዛቸውን በፍጥነት መፈጸም ማንኛውንም የማይፈልጉትን ነገር መተው ተገቢ ነው።
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት