Weight | 117 g |
---|
Miscellaneous
የኢስላም ድል አድራጊነት
4.00 $
ኢስላም በሁሉም መስኩ ድል አድራጊ የሆነ ሃይማኖት ነው፡፡ ብሥራት ነጋሪ እንጂ በታኝ አይደለም፡፡ አግራሪ እንጂ አጥባቂ እንዳይሆን ታዝዟል፡፡ ይህ በስድስት ምዕራፎች ተከፋፍሎ ለንባብ የበቃው መጽሐፍ ትልቅ ተስፋን በሚያጭር መልኩ የኢስላምን ድል አድራጊነት ይነግረናል፡፡ በአምስቱ ምዕራፎች የቁርኣን፣ የሐዲስ፣ የታሪክ፣ የተጨባጭ እውነታና የመለኮታዊ ሕይወት ሕግጋት ብስራትን ሊያስረዳን በስድስተኛው ምዕራፍ ደግሞ ለተዛቡ ግንዛቤዎች የተዳረጉ ሐዲሶችን ይተነትንልናል፡፡
አዘጋጅ ፡ ኢማም ፕ/ር ዩሱፍ አልቀርዷዊ
ትርጉምና ፡ አምባሳደር ኡስታዝ ሐሰን ታጁ
የታተመበት ዓመት ፡ ሐምሌ 199
የገጽ ብዛት ፡ 112
ከመጽሐፉ ፡ – ጥሩ አማኞች በዚህች ምድር ላይ ከኢስላም አንፃር በሚያዩትና በሚሰሙት ነገር ከቶዉኑ ተስፋ የሚቆርጡ አይደሉም፤ ሊቆርጡም አይገባም፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) ሙእሚኖችን ሁሌም ቢሆን ሊረዳ ቃል ገብቷል፡፡ ከቁርኣን ብሥራቶች መካከል አላህ ለሙእሚኖች ድልንና ስኬትን እንደሚለግስ፣ ለነርሱ ተገንና ጋሻ እንደሚሆን፣ እንደሚወዳጃቸው፣ እንደሚያቀርባቸው፣ እንደሚረዳቸው፣ ምንጊዜም አብሯቸው እንደሆነ ቃል መግባቱን የሚያመለክቱ አንቀፆች ይገኙባቸዋል፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት