የኢስላም ሁለንተናዊነት ክፍል አንድ

1.00 $

ኢስላም ሰማያዊዉን ዓለም ለመውረስ ብቻ የሚከተሉት ሃይማኖት  አይደለም፡፡ ኢስላም የዚህንም ሆነ የመጨረሻዉን ዓለም ስኬት የሚጠቁም ሁለገብ መመርያ ነው፡፡ ኢስላም ሁሉ አቀፍና ሁለንተናዊ ነው፡፡ የሰዉን ልጅ የሕይወት ጎኖች ሁሉ ይዳስሳል፡፡ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሥነልቦናዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሁሉንም ይነካካል፡፡ ይህ መጽሐፍ የተለያዩ ጉዳዮችን በማንሳት የኢስላምን ሁለንተናዊነት ጠለቅ ባለ ሁኔታ ይዳስሳል፡፡ ኢስላም ከሳይንስና ከፖለቲካ አንፃር ያለው እይታ በስፋት የቀረበበት በሁለት ክፍሎች የቀረበ መጽሐፍ ነው፡፡
አዘጋጅ ፡ ዶ/ር ዐብደላህ አልቀሕጣኒ
ትርጉምና ዝግጅት ፡ አሕመድ ሑሴን (አቡ ቢላል)
የገጽ ብዛት ፡ ቁ.1 88 ገጽ  እና ቁ.2  140 ገጽ
ከመጽሐፉ ፡
ሙስሊሞች ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ እግዚአብሔር ልጅ ሳይሆን እንደ ነቢይ ይቀበሉታል። የማርያምን የኢየሱስ እናትነት ይቀበላሉ። አዳምን፣ ኖህን፣ አብረሃምን፣ ሙሴን፣ ያዕቆብን ያውቃሉ። የመንግስተ ሰማያትንና የገሃነምን ጽንስ ሐሳብ ያምናሉ። መንግስተ ሰማያት በረሃ ያልሆነ አትክልትና ወንዞች የሚፈስሱበት እንደሆነ፣ ገሃነም ደግሞ ኃጢያተኞች ቆዳቸው እስኪላጥ ድረስ የቀለጠ ብረት የሚጠጡበትና የዘላለም አካላዊና አእምሮአዊ ስቃይ የሚከፍሉበት እንደሆነ ይቀበላሉ።
እስልምናና ክርስትና የመነጩት በአንድ አንድ ሰው አማካይነት ሲሆን ትልቁ ልዩነት ….
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: