የኢማን ድክመት

1.00 $

ባለንበት ዘመናዊ የተባለ ዓለም ከዒባዳ የሚያራርቁ ብዙ ነገሮች እየተፈጠሩ ነው፡፡ የሰው ልጅ ለኑሮው በሚያደርገው ውጣ ውረድ ሸሪዓው የማይፈቅደውን ብዙ ነገር ያደርጋል ይዋሻል፣ ይቀጥፋል፣ ያታልላል… ቀልብን የሚያደርቁም ብዙ ነገሮች በዙሪያችን ተበራክተዋል፡፡ ጠንካራ ሰው ማለት እነዚህን ፈተናዎችን በድል አጠናቅቆ በሥርዓቱ አላህን መግገዛት የቻለ ነው፡፡ ኢማን ደግሞ ይጨምራል ይቀንሳል፡፡ አዘጋጁ ይኸው የውጣ ውረድ ዓለምንና ኢማንን ነው በብዕራቸው የፈተሹት፡፡
አዘጋጅ ፡ ሸህ ሙሐመድ ሷሊሕ አልሙነጃድ
ትርጉም ፡ አብይ ጣሰው
የገጽ ብዛት ፡ 80
የታተመበት ዓመት ፡ ሐምሌ 2002
ከመጽሐፉ ፡ በአሁኑ ወቅት ሁላችንም ማለት ይቻላል እርጋታ አጥተናል። በኑሮአችን፣ በምንሠራው ሥራ፣ በትዳራችንና በሁሉም የሕይወት መስካችን ደስታ ከሸሸን ቆይቷል። ወጣቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ካፌዎችን እያጣበቡ መጥተዋል። ነገር ግን የፈለጉትን ደስታ ማግኘት ተስኗቸዋል። መስጊድ የገባውም ከመስማማት ይልቅ መናቆርን መርጧል። በሁሉም አቅጣጫ የሚያስደስት ነገር ማግኘት እየከበደ መጥቷል። “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንዲሉ የሙስሊሙ ኡምማ በአጠቃላይ ሽንፈት ውስጥ ይዳክራል። የዚህ ሁሉ መንስኤ ከአላህ (ሱ.ወ) ጋር ያለን ግንኙነት ደካማ በመሆኑ ነው።
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: