የኢማም ነወዊ አርባ ሐዲሥ

3.00 $

ይህኛው መጽሐፍ ከቀደመው አርባ ሐዲሥ የሚለየው ማብራሪያ የተዘጋጀለት መሆኑ ነው፡፡ ትርጉሙ እንዳለ ሆነ ሙሐመድ ሰዒድ ማብሪሪያዉን ሠርቶለታል፡፡
አዘጋጅ ፡ ኢማም አን-ነወዊ
ትርጉም ፡ ዶ/ር ኢድሪስ ሙሐመድ
ማብራሪያ ፡ ሙሐመድ ሰዒድ
የገጽ ብዛት ፡ 112

የታተመበት ዓመት ፡ መጋቢት 2010
ከመጽሐፉ ፡
አቡ ሙሐመድ ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምር ኢብኑልዓስ (ረ.ዐንሁማ) እንደአወሩት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “ዝንባሌያችሁ እኔ የመጣሁበትን መንገድ (ሕገ ኢስላምን) እስካልተከተለ ድረስ እምነት የላችሁም፡፡” የተጣራ ሰነድ በኪታቡል ሁጃ የተጠቀሰ ሶሒሕ ሐዲሥ፡፡
ከሐዲሡ እንደምንረዳው ሙስሊም የሆነ ሰው እስልምናን ሙሉ በሙሉ ውስጡ ገብቶ መኖር ይኖርበታል፡፡ አንድ ሰው በትክክል አመነ ሊባል የሚችለውም በሙሉ ህይወቱ በዝንባሌውም ሆነ በድርጊቱ ሁሉ የአላህን እና የመልዕክተኛውን መንገድ የተከተለ እንደሆነ ነው፡፡ ሀሳቡና ፍላጎቱ ጭምር ከሃይማኖቱን ፍላጎት መውጣት የለበትም፡፡ በስሜቱ የዲኑን ስሜት መከተል፣ በፍላጎቱም የሃይማኖቱን ፍላጎት ማንፀባረቅ አለበት፡፡ ማጣቀሻውም ሆነ መመለሻው፤ ከፊት ሆኖም የሚመራው ሃይማኖቱና አስተምህሮው ሊሆን ይገባል፡፡ ለስሜቱና ለዝንባሌው ሲል ከመስመሩ ማፈንገጥ የለበትም፡፡ ይህን ፈትሾ ስሜቱ ከዲኑ ስሜት ጋር የተጣጣመ መሆኑን ካወቀ በርግጥ ያኔ በትክክል አምኗል ማለት ይቻላል፡፡
አሳታሚ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: