የአፍቃሪዎች ዓለም

4.00 $

ፍቅር አላህ (ሱ.ወ) ለሰው ልጆችና ለእንስሳትም ጭምር በተፈጥሮ የለገሰው ታላቅ ፀጋ ነው፡፡ ፍቅር በሰው ልጆች መካከል ብቻ የማይወሰን፣ ፈጣሪንና ተፈጥሮን ማፍቀርን ጭምር የሚያጠቃልል ኃያል ስሜትና ተግባር ሆኖ እያለ ብዙውን ጊዜ በተለይም በተቃራኒ ፆታዎች መካከል ያለው ተፈጥሯዊና ስሜታዊ መፈላለግ ብቻ ፍቅር ተደርጎ ሲቀርብ ይስተዋላል፡፡ ይህ እጅግ የተሳሳተ ግንዛቤና አቀራረብ ነው፡፡ በኢስላማዊ አስተምህሮ ግን ፍቅር ዘርፈ ብዙ ሲሆን የመጀመሪያውና ፍጹማዊ ፍቅር የውበትና የምልኡነት ምንጭ የሆነውን ታላቁን ፈጣሪ ማፍቀር ነው፤ ፍቅር ሁሉ ከዚህ ፍቅር ይመነጫል፡፡ መጽሐፉ በአጠቃላይ ስለ ፍቅር ምንነትና መገለጫዎች ያወሳል፡፡ ስለ ፍቅር አስደናቂ ወጎችም ይዳስሳል፡፡ ያላስተዋልናቸዉን ጎኖችም ያስመለክታል፡፡ መጽሐፉ ‹‹ረውደቱል ሙሒቢይን ወ ኑዝሀቱል ሙተቂይን›› የተሠኘው የታላቁ ዓሊም የኢማም ኢብኑ ልቀይም አልጀውዚይ ሥራ ነው፡፡ ተርጓሚው አሳጥሮና ጨምቆ ለአገራችን አንባቢያን በሚመች መልኩ አቅርቦታል፡፡
ዝግጅት ፡ ኢማም ኢብኑል ቀይም
ትርጉም ፡ ጁነይድ ዐብዱልመንናን
የገጽ ብዛት ፡ 127
የታተመበት ዓመት ፡ ሚያዚያ 2007
ከመጽሐፉ ፡
ከአፍቃሪዎችም መካከል አላህን የሚያፈቅሩ፣ ጣዖትን የሚያፈቅሩ፤ አገርን አፍቃሪዎች፣ ጓደኛን የሚያፈቅሩ፣ ቤት የሚያፈቅሩ፣ ልጆችን የሚያፈቅሩ፣ ገንዘብን የሚያፈቅሩ፣ ኢማንን የሚያፈቅሩ፣ ቁርኣንን የሚያፈቅሩ አለ፡፡
አላህ (ሱ.ወ) እርሱን፣ መጽሐፉንና መልዕክተኛውን አፍቃሪዎች ከሌሎች አፍቃሪዎች ሁሉ የበላይ አድርጓቸዋል፡፡
በፍቅርና ለፍቅር ሲባል ሰማይና መሬት ተፈጠረ፤ በውስጣቸውም ፍጡራን ተሞሉ፡፡ የሰማይ አካላትም ሁሉ በፍቅር ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በፍቅር ሁሉም ነገር ተጀምሮ ያልቃል፡፡ በፍቅር ኃይል ልብ ፍላጎቱን ያገኛል፡፡ ከችግርም ይላቀቃል፡፡ ወደ ጌታውም ያመራል፡፡ የኢማንን ቃናም ያጣጥማል፡፡ …

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 128 g