Weight | 92 g |
---|
የአደብ አስፈላጊነት
3.00 $
የአደብ (ሥርዓት) ጉዳይ ከጊዜ ወደጊዜ በእጅጉ አሳሳቢ ሆኗል፡፡ ሰዎች በሥልጣኔ ከፍ አልን ባሉ ቁጥር ለሥርዓት ግዴለሽ ሆነዋል፡፡ የሰው ልጅ ኑሮ የደመነፍስ ሆኗል፡፡ ማን ከማን ይበልጣል በሚል ስሜት ሁሉም እኩል እየተያየ ነው፡፡ ሁሉንም እንደየደረጃው ያለማስቀመጥ ችግር ብዙ ቦታ ላይ ይስተዋላል፡፡ የሥርኣት መዛባት፣ የነገሮች መመሰቃቀል፣ የቅደምተከተል መታጣት በሰፊው እየተስተዋለ ነው፡፡ ትልቅ አይከበርም፤ ትንሽ አይታዘንለትም፡፡ የሃይማኖት አባቶችና ዓሊሞች እየተደፈሩ ነው፡፡ ኢስላም የሰው ልጅ ሁሉ እንዲከበር ያዛል፡፡ የክብር ባለቤቶችም ክብራቸው እንዳይገፈፍ ያሳስባል፡፡ ዘመናችን በብዙ ነገሮች ዉስጥ አደብ የሚያስፈልግበት ነው፡፡ የዚህች መጽሐፍ አንኳር መልዕክት “አደብ -ውብ ባሕሪያትን መላበስና በዘላለማዊ መርሆዎች መታነፅ” ነው፡፡
አዘጋጅ ፡ ዶ/ር ሙሐመድ ሙሳ አሽ-ሸሪፍ
ትርጉም ፡ ዐብዱልከሪም ታጁ
የገጽ ብዛት ፡ 88
የታተመበት ዓመት ፡ 2008
ጥቂት ከመጽሐፉ ፡
በነፍሱ ላይ ጉድለቶች መኖራቸውን የተገነዘበ ሰው፤ ነፍሱ በአደብ ልጓም እስክትያዝና ተገዥ እስክትሆን ድረስ ሊያሰለጥናት፣ ሊገራትና ሊታገላት ይገባል፡፡ ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው በተፈጥሮው አደብን አይላበስም፤ መንገዶችን አያውቅም፡፡ ስለዚህ ራሱን መታገል አለበት፡፡ አደብ ተፍጥሯዊ ባህሪው እስኪመስል ድረስ ነፍሱን መግራትና ማሰልጠን አለበት፡፡
አንድ ሰው ስለ አደብ ማወቁ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ የአደብን ምንነት መገንዘቡ ብቻ ፋይዳ የለውም፡፡ ባህሪው ለማድረግ መታገል፣ ራሱን ማለማመድ፣ ነፍሱን መግራትና ማሰልጠን ይጠበቅበታል፡፡
ኢማም አል-ገዛሊ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡- “ለረጅም ጊዜ ከሥራ ርቆ የቆየ ሰው፣ ስንፍና እንደሚያሸንፈው እወቅ፡፡ ነፍሱን በማጥራት ዓላማ የሚፈለገውን ጥረት ማድረግና ራሱን ማለማመድ፣ ባህሪውን ለመለወጥ በሥራ መጠመድ ወ.ዘ.ተ. እንደ ተራራ ገዝፎ ይታየዋል፡፡ ውስጡ ተበላሽቷልና ነፍስያው ይህን እንዲያደርግ አትፈቅድለትም፡፡ በቃ፣ ባህሪ አይቀየርም፤ ጠባይ አይለወጥም ከሚል ድምዳሜ ላይ ይደርሳል፡፡” ብለዋል፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት