የአኗኗር ጥበብ

3.00 $

መጽሐፉ ከ እስከ የተለያዩ የአኗኗር ጥበቦችን ያስተምራል፤ ከሁሉም የሰው ልጆች ጋር በምን መልኩ መኖር እንደሚቻል፤ ከሰዎች ጋር የሚኖረን ግንኙነት በምን መልኩ መሆን እንዳለበት፣ ስሜታቸዉንና ፍላጎታቸዉን እንዴት እንደምንረዳ፣ ሞራላቸውን በምን መልኩ መጠበቅ እንዳለብን፣ ስለ ሚስጢር መጠበቅ፣ ከወላጆች ጋር ሊኖረን ስለሚገባ ግንኙነት፣ ስለ መልካም ሥነምግባራት አስፈላጊነት፣ ስለ መመካከርና ስለ ሌሎችም ያወሳል፡፡
አዘጋጅ ፡ ዶ/ር ሙሐመድ ዐብዱረሕማን አል-ዐሪፊ
ትርጉምና ጥንቅር ፡ ሙስጦፋ ሓሚድ ዩሱፍ
የገጽ ብዛት- 88
የታተመበት ዓመት ፡ የካቲት 2006
ከመጽሐፉ ፡ የሰዎችን ስሜት መጠበቅ አዲስ ቁስል እንደማከም ነው፡፡ አንድ ሰው አንዳች ነገር ተናግረነው ወዲያዉኑ ሊሰማው ይችላል፡፡ ከንግግራችን በኋላ ግለሰቡን ስንመለከት ንግግራችን ስሜቱን የጎዳ መስሎ ከታየን ነገሮች ተባብሰው መጥፎ ደረጃ ላይ ከመድረሳቸው በፊት የግለሰቡ ስሜት ሊያገግም የሚችልበትን አፋጣኝ ዘዴ መቀየስ ይኖርብናል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) የሰዎችን ስት ለመጠበቅ በጣም ይጨነቁ ነበር ….

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 88 g