የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ተዓምራት

2.00 $

አላህ (ሱ.ወ.) ከሕዝቦች መካከል ነቢያትን መርጦ ሲልክ ተዓምራችን አስይዞ ነው፡፡ ለነቢያችን ሙሐመድም በርካታ ተዓምራትን ሠጥቷቸዋል፡፡
የነቢዩን መልዕክተኝነት ከሚያረጋግጡ ተዓምራት መካከል ንጹሕ ሥነ-ምግባራቸው፣ የተሟላ ስብዕናቸው፣ ጀግንነታቸው፣ ታጋሽነታቸው፣ ችሮታቸው፣ ለዓለማዊ ጸጋ አለመጓጓታቸው፣ ከሰዎች አለመፈለጋቸው፣ ከባልንጆሮቻቸው ጋር የነበራቸው መልካም ግንኙነት፣ እውነተኛነታቸው፣ ታማኝነታቸው… ይገኙበታል፡፡ እነዚህንና ሌሎችንም ተዓምራቶች በዚህ በተተረጎመው መጽሐፍ ዉስጥ ያገኙታል፡፡

ዝግጅት ፡ አቡልፊዳእ ኢስማዒል ኢብኑ ከሢር
ትርጉም ፡ አምባሳደር ኡስታዝ ሐሰን ታጁ
የገጽ ብዛት ፡ 183
የታተመበት ዓመት ፡ ጥቅምት 2000
ከመጽሐፉ ፡ ለነቢዩ ከተሠጡት ተዓምራት ሁሉ ቁርኣን አውራ ነው፡፡ እጅግ ግልጽና ብሩህ፤ እጅግ ማራኪ የሆነ መረጃም ነው፡፡ አወቃቀሩ የሰው ልጆችም ሆነ አጋንንት የሚሞክሩት አይደሉም፡፡ መሰሉን ሊያመጡ ፈጽሞ አይቻላቸዉም፡፡ አላህም በዚሁ ፈትኗቸው ብዙ ቢሞክሩም የተሳካለት የለም … ቁርኣን በርግጥም ለታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) የተሠጠ ዝንታለም የሚገዳደረው የሌለ ትልቅ አዕምሯዊ ተዓምራት ነው፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 38 g