የነቢያት ታሪክ

9.00 $

አላህ (ሱ.ወ.) በተለያየ ዘመን የተለያዩ ነቢያቶችን ወደ ሰው ልጆች ልኳል፡፡ ነቢያት የአላህን (ሱ.ወ.) መልዕክት ለሰው ልጆች ያደርሱ ዘንድ ከሰው ልጆች መካከል የተመረጡ ናቸው፡፡ ከአባታችን አደም (ዐ.ሰ.) ጀምሮ በርካታ ነቢያት ወደ ሰው ልጆች ተልከዋል፡፡ በቁጥር ከ124ሺህ በላይ እንደሆኑ ይነገራል፡፡ በቁርኣን ዉስጥም ሀያ አራት ነቢያትና መልዕክተኞች በሥም ተጠቅሰዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ ሁለት ክፍሎች ያሉት ሲሆን ከ300 በላይ የመመዘኛ ጥያቄዎችንም አካቷል፡፡ መጽሐፉ በዋነኛነት የነቢያት የሕይወት ታሪክን ይዳስሳል፡፡
አዘጋጅ ፡ ዑሥማን ኑሪ ቶፕባሽ
ትርጉም፡ ዐብዱልከሪም ታጁ
የገጽ ብዛት ፡ 532

የታተመበት ዓመት ፡ 2008
ከመጽሐፉ ፡
መድየን ዮርዳኖስ ውስጥ በሚገኘው የዐቀባ የባህር ወሽመጥ እና ሶሪያ በሚገኘው የሒምስ ሸለቆ መካከል የምትገኝ ቦታ ናት፡፡ ‹መድየን› የሚለውን ስም ያገኘችው በዚያ አካባቢ ነዋሪ ከሆነች ጎሳ ነበር፡፡ የመድየን ሰዎች አላህን (ሱ.ወ) ማምለክ እና መገዛት አቆሙ፡፡ በጥመትና በኃጢያት ውስጥ ተነከሩ፡፡ ለጣዖታት መስገድ ጀመሩ፡፡ የንግድ ቅፍለቶች በመድየን በኩል ያልፉ ስለነበር የህዝቦቿ የገቢ ምንጭ ንግድ ነበር፡፡ በሥራ አዋቂነታቸው ይደነቁ ነበር፡፡ መፍጠር የሚችሉ ‹መለኞች› ተደርገው ይታዩ ነበር፡፡ ዕቃ ሲገዙ ሚዛን ያጎድላሉ፣ ክብደት ይቀንሳሉ፤ ስለዚህ ትንሽ ገንዘብ ይከፍላሉ፡፡ ሲሸጡ ደግሞ ያከብዱታል፡፡ ጎደሎ ዕቃ በመሸጥ አላግባብ ገንዘብ ያገኙበታል፡፡ በተለይ ይህን የሚያደርጉት እንግዳ እና መጤ ከሆኑ ሰዎች ላይ ነው፡፡ ይመካከሩባቸዋል፡፡ በተለያየ ዘዴ ንብረታቸውን ይነጥቋቸዋል፡፡ በዚህ መልኩ በሥራም ይሁን በሌላ መንገድ ያገኙትን ሁሉ ያወናብዳሉ፤ ይበድላሉ፡፡

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 489 g