የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) ሚስቶች ታሪክ

3.00 $

ነቢያዊው ቤት የሁሉም ቤቶች ተምሳሌት ነው፡፡ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ሚስቶችም እናቶቻችን ናቸው፡፡ የርሣቸዉ ሚስቶች በመሆናቸዉም የተከበሩ ናቸው፡፡ ይህ በርግጥም ትልቅ መታደል ነው፡፡ ስለነርሱ ማወቅ የሕይወት ታሪካቸዉን ማንበብ፣ ስብእናቸዉን ማስተዋል .. ብዙ የሚያስገኙልን ጥቅሞች ይኖሩታል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) የተዋጣለት አባወራ ናቸው፡፡ ሚስቶቻቸዉን ይወዳሉ፣ ያግዛሉ፣ ይንከባከባሉ፡፡
ጥንቅርና ትርጉም ፡ አወድ ዐብዱሶቡር
የገጽ ብዛት ፡ 88
የታተመበት ዓመት ፡ ግንቦት 2004
ከመጽሐፉ ፡ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) ከልባቸው የሚወዷትና የሚያከብሯት የመጀመርያ ሚስታቸው ኸዲጃ (ረ.ዐ.) በሞት ስትለያቸው፤ ቤታቸው ሰው የማይኖርበት እስኪመስል ድረስ ባዶነት አጥልቶበት ነበር፡፡ ይህን የተገነዘበችው ዘመዳቸው ኸውለትም የቀዘቀዘው ቤታቸው በድጋሜ ሕይወት ይዘራበትና ለልጆቻቸዉም እናት እንድትሆንላቸው ብላ ሰውዳእ የምትባልን ሴት አጨችላቸው፡፡ ሰወዳእ ቢንት ዘምዓ …

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: