የነቢዩላህ ዩሱፍ (ዐ.ሰ) ታሪክ

3.00 $

በቁርኣን ዉስጥ ከተጠቀሱ እጅግ አስደማሚ የነቢያት ታሪኮች መካከል አንዱ የነቢየላህ ዩሱፍ ታሪክ ነው፡፡ የነብዩላህ ዩሱፍ (ዐ.ሰ) ታሪክ በመላው ዓለም በመጽሐፍ፣ በፊልም፣ በካርቱን ፊልም በተለያዩ መንገዶች ለአንባቢያን ሲደርስ ቆይቷል፡፡ በወንድሞቻቸው በደል በውሃ ጉድጓድ ተጥለው፣ ኋላም ከዚያ አላህ አወጣቸዉና ወደሚወዱት አባታቸው ሳይመለሱ በባርነት ወደ ግብጽ አገር ተሸጋግረው ተሸጡ፡፡ እዚያም ከብዙ መከራና ስቃይ በኋላ የግብጽ ሚኒስትር እስከመሆን ደረሱ፡፡ የርሣቸው ታሪክ እጅግ አስተማሪ ሲሆን በዋናነትም ጽናትን፣ ብርታትን፣ ትዕግስትን፣ መከራን መቋቋም… እና ሌሎች በርካታ ቁም ነገሮችን እናገኝበታለን፡፡ የመጽሐፉ አዘጋጅም የተለያዩ መረጃዎችን በማጠናቀር ውብ በሆነ መንገድ ትረካውን ያስነብበናል፡፡
አዘጋጁ ታሪኩን ለአንድ ዓመት ያህል በአል-ኢስላም መጽሔት ለአንባቢያን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡
አዘጋጅ ፡ ሚፍታሕ ሰዒድ
የገጽ ብዛት ፡ 160
የታተመበት ዓመት ፡ የካቲት 2005
ከመጽሐፉ ፡ ነቢየላህ የዕቁብ (ዐ.ሰ.) ልጃቸዉን ዩሱፍን (ዐ.ሰ.) አጥብቀው መውደድ የጀመሩት ገና የሁለት ዓመት ሕፃን እያሉ ነበር፡፡ ዩሱፍም አስገራሚዉን ህልም የተመለከቱት የአሥራ ሰባት ዓመት ታዳጊ በነበሩበት ወቅት ነበር፡፡ ፀሐይ ከአድማሱ ግርጌ ሥር ሆና ተስፈንጣሪ ጨረሮቿን በመላክ በጠዋት ግርማ ሞገሷ ለመዳሰስ እየሞከረች ነው፡፡ ታዳጊው ዩሱፍ ከእንቅልፉ በነቃ ወቅትም ባለመው ህልም ፊቱ በደስታ ፈክቶ ወደ አባቱ ሮጠ፡፡ ያየዉንም ይተርክ ጀመር …
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: