የተወዳጁ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ.) ፈገግታዎች

$3.00

መጽሐፉ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ፈገግ ያሉባቸውን የተለያዩ ሁኔታዎች፣ ክስተቶች፣ ገጠመኞች፣ የሰዎች አነጋገሮችንና ሌሎችንም እየተከታተለ ያስቃኘናል፡፡ ተወዳጁ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ.) በተለይ ከሶሓቦቻቸው ጋር ምን ያህል ተግባቢ፣ ተጫዋችና በነርሱ ውስጥም ደስታን ለመፍጠር ምን ያህል ይጥሩ እንደነበርም እናይበታለን፡፡ ከልጅም ሆነ ከአዋቂ ጋር እንዴት ይቀራረቡ እንደነበርም ትምህርት እንወስድበታለን፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ፈገግ ባሉ ቁጥር አብረን ፈገግ መሰኘታችን አይቀሬ ነው፡፡ ሐቢቢ ፈገግ ሲሉ አብረን እንፈግጋለን!!
አዘጋጅ – ሙሐመድ ዐሊ ዑሥማን
ትርጉም – አሕመድ ሑሴን (አቡ ቢላል)
የገጽ ብዛት ፡ 71
የታተመበት ዓመት ፡ 2002
ከመጽሐፉ በጥቂቱ ፡
ዓኢሻ (ረ.ዐ.) ባወሩት ሐዲስ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከተቡክ ወይም ከኸይበር ዘመቻ እንደተመለሱ ወደ ቤት ሲገቡ ግርዶዋን ነፋስ በኃይል ሲገልበው በመደርደሪያዋ ላይ የመጫወቻ አሻንጉሊቶቿ ተጋለጡ፡፡ ይህን ያስተዋሉት ነቢዩ ዓኢሻ ሆይ! እነዚህ ምንድን ናቸው;” አሏት፡፡ እርሷም “አሻንጉሊቶቼ ናቸው” በማለት መልስ ሰጠች፡፡ ከአሻንጉሊቶቹ ውስጥ ከጨርቅ የተሰፋና ሁለት ክንፎች ያሉት ፈረስ ያዩት ነቢዩ “ይህ ከመካከላቸው የምመለከተው ምንድን ነው?” በማለት ጠየቋት፡፡ `ፈረስ ነው” አለች፡፡ `እነዚያ ነገሮች ታዲያ ምንድን ናቸው;” አሏት ከጐንና ከጐኑ ያሉትን ቅጥያዎች እያስተዋሉ፡፡ “ሁለት ክንፎች” በማለት መለሰች፡፡ `ሁለት ክንፎች ያሉት ፈረስ;’’ አሉ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.)፡፡ `ነቢዩ ሱለይማን ሁለት ክንፍ ያለው ፈረስ እንደነበራቸው አያውቁምን;” በማለት ዓኢሻ ጥያቄያቸውን በጥያቄ መለሰች፡፡ በዚህ ጊዜ ነቢየ (ሰ.ዐ.ወ) የክራንቻ ጥርሶቻቸው እስኪታዩ ድረስ ፈገግ አሉ፡፡
ጃቢርን (ረ.ዐ.) ዋቢ በማድረግ በተላለፈ ሐዲሥ አንድ ሰው ወደ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ በመምጣት ተኝቼ ሳለሁ (በህልሜ) ጭንቅላቴ ሲቆረጥ (አንገቴ ሲቀላ) አየሁ፡፡’’ አላቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ፈገግ ብለው በማለት ፡-አንዳችሁ በተኛበት ሰይጣን ከተጫወተበት ያንን ለሰዎች አይናገር፡፡” አሉ፡፡

Category: