Weight | 331 g |
---|
የቤተሰብ ህይወት በኢስላም
$4.00
መጽሐፉ ኢስላማዊ ቤተሰብ ላይ ያተኩራል፤ በኢስላም የቤተሰብ ዓላማ ምን እንደሆነ፣ ይህ ታላቅ ተቋም ምን መምሰልና በምን መልኩ መገንባት እንዳለበት፣ ወደተቋሙ የሚገቡ አዳዲስ አባላት ሊያውቁ ስለሚገቡ ጉዳዮች፣ በቤተሰብ ሕይወት ዉስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው፣ ስለ ትዳር አጋሮች ሚናና ኃላፊነት፣ ስለ ልጆች አስተዳደግ፣ ስለ ጋብቻ ዉል ማፍረስ ሥርዓቶችና ስለለሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች፣ ቁርኣንና ሐዲሥን እንዲሁም የተለያዩ ጥናቶችን መሠረት በማድረግ በሰፊው ይዘረዝራል፡፡
አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ዑመር
የገጽ ብዛት ፡ 360
የታተመበት ዓመት ፡ መስከረም 2000
ከመጽሐፉ ፡
በኢስላም ሸሪዓ ትዳርን መመስረት የኢማን አካል፣ የተፈጥሮ መንገድ፣ የፈጣሪ ትዕዛዝ ነው። ጋብቻ የሰው ልጅ ምድራዊ ተልዕኮውን ለማሳካት የመሰረት ድንጋይ አድርጎ የሚገለገልበት ቀዳሚ ተቋም ነው። ጋብቻ ማለት ሁለትን የተከበሩ የአደም ልጆች በአንድ ዓላማ፣ በአንድ ቤት፣ በአንድ ፍራሽ፣ በአንድ ስሜት፣ በአንድ ምስጢር፣ በአንድ አመለካከት፣ በአንድ ዓይነት ሃዘንና ደስታ፣ በአንድ ዓይነት ክስረትና ስኬት፣ ለአንድ ግብ መስዋዕትነትን መክፈል፣ ለአንድ ዓላማ ተጠያቂነትና ኃላፊነት እንዲኖራቸው ያደረገና እንዲሁም አንድ አካል እንዲሆኑ ያስቻለ ብቸኛው ምድራዊ ኃይል ነው።
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት