የሶላት መማሪያ

2.00 $

ሶላት ከአምስቱ የእስልምና መሠረቶች መካከል አንዷ ናት፡፡ ሶላት የኢስላም ምሰሶ ናት፡፡ ሶላት ሙስሊም እና ሙስሊም ያልሆነዉን መለያ ናት፡፡ ማንኛዉም ሙስሊም በቀን ዉስጥ የአምስት ወቅት ሶላት ግዴታ አለበት፡፡ ግዴታዉን ይፈጽ ዘንድ ስለ ሶላት አሰጋገድ ማወቅ ይኖርበታል፡፡ ይህ መጽሐፍ በስዕላዊ መግለጫ በማስደገፍ ጭምር ስለ ሶላት አሰጋገድ ያብራራል፡፡
ጥንቅር ፡ ዐብዱልሐኪም
የገጽ ብዛት ፡ 88
የታተመበት ዓመት ፡ 1988
ጥቂት ከመጽሐፉ ፡
ሶላት ቅርፅና ይዘት አላት፡፡ ቅርጹ ተገቢ የአካላት እንቅስቃሴ ሲሆን፥ ይዘቱ (መንፈሱ) ደግሞ የቀልብ (ልቦና) ወደ አላህ መቃናትን የሚጠቁም ነው፡፡ ሶላት አካላዊና መንፈሳዊ ጂምናስቲክ ነው፡፡ መንፈስ በሶላት ታድገለች፡፡ የሰውን ልጅ ከፈጣሪው የሚያገናኝ መስመርም ሶላት ነው፡፡ ሶላትን መተው ወይም መዘንጋት ደግሞ ከአላህ (ሱ.ወ) ጋር መቆራረጥ ነው —ከእዝነቱ መራቅ፡፡ ውለታ ቢስነትም ነው፡፡
ሥርዓቱን የጠበቀ ትክክለኛ ሶላት ለተለያዩ የቀልብ በሽታዎች ፍቱን መድኃኒትና የወንጀል ማፅጃም ዋነኛ መንገድ ነው፡፡

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: