Weight | 119 g |
---|
የሴቶች ደረጃ በኢስላም
$2.00
ኢስላም ለሴት ልጅ ትልቅ ክብር ሠጥቷል፡፡ ሴት ልጅ የሕብረተሰቡ ግማሽ አካል እንደሆነችም ይገነዘባል፡፡ ሴት ማለት እናት፣ እህት፣ ሚስት፣ ልጅ … ናት፡፡ በቁጥር ግማሽ የኅብረተሰቡ አካል ብትሆንም በሚና ግን ከግማሽ በላይ ናት ይላሉ ዶ/ር ዩሱፍ አልቀርዷዊ፡፡ ቁርኣን ሴትን ልጅ እንዴት እንዳከበራትና እንዳላቃት ማስረጃ እየጠቀሱ ያስነብቡናል፡፡ የመማር የማወቅ መብቷን፣ የፈለገችውን የማግባት መብቷን፣ በቤት ውስጥ ያለመታሰር ነጻነቷንና ሌሎችንም ያብራሩልናል፡፡
አዘጋጅ ፡ ፕ/ር ኢማም ዩሱፍ አልቀረዷዊ
ትርጉም ፡ አምባሳደር ኡስታዝ ሐሰን ታጁ
የገጽ ብዛት ፡ 138
የታተመበት ዓመት ፡ ጳጉሜ 1999
ከመጽሐፉ ፡ ኢስላም ለሴት ልጅ እንስታዊ ባሕሪ ከፍተኛ ክብር ሰጥቷል። የወንድ ማሟያ እንደሆነችም አስተምሯል። ወንዱም የርሷ ማሟያ ነው። አንዱ የሌላኛው ባላንጣ ወይም ተፎካካሪ አይደለም። ስብዕናው የተሟላ ይሆን ዘንድ አጋዥ የሚሆን እንጅ። “ጣምራነት” የፍጡራን ባሕሪ እንዲሆን የአላህ ፈቃድ ሆኗል። በሰው፣ በእንስሳትና በዕፅዋት ዓለም ውስጥ እንስትና ተባዕት እናገኛለን። በኤሌክትሪክ፣ በማግኔትና ሌሎችም የግዑዛን ዓለም ውስጥ ደግሞ “ፖዘቲቭ” እና “ኔጌቲቭ” ባሕሪያትን እናገኛለን። አተም እንኳ “ኤሌክትሮን” እና “ፕሮቶን” የተባሉ የተለያዩ ቻርጅ (ባሕሪ) ያላቸው ክፍሎች አሏት። ….
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት