የረመዳን ወርና የጾም ሥርኣት

3.00 $

ረመዷን ታላቅ እና ልዩ የሆነ ወር ነው፡፡ ይህ መጽሐፍም ስለ ረመዷን ወር ታላቅነት፣ ስለ ጾም ትሩፋት፣ ሥርኣቶች፣ የጾም ዓይነቶችና ሌሎችም የተካተቱበት ነው፡፡ የሰው ልጅ ትዕግሥትን፣ ጽናትን፣ ስሜት መቆጣጠርና መግዛትን የሚችለው በጾም ወቅት ነው፡፡ ጾም ሥነ-ምግባርን ያስተምራል፤ ለጤና ይጠቅማል፡፡ ከዚህም ባሻገር ዋናውና መሠረታዊው ጉዳይ ፆም አንዲ የአምልኮ መንገድ ነው፡፡ በመፆም አላህን እናመልካለን ለትዕዛዙ እናድራለን፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ የረመዷን ወረ ፆም ምን ዓይነት ሥርዓት አለው? ለሚለው ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ዝርዝር ማብራሪያ ይሰጣል፡፡ እነማን መቼ እንዴት ይፆማሉ?፡፡ እነማንስ መቼ እንዴት አይፆሙም? በፆም ወቅት ምን ምን ዓይነት ተግባራት ይጠበቅብናል? ሁሉንም የፆም ጥያቄዎች መጽሐፉ መልስ ይሰጣል፡፡
አዘጋጅ/ ትርጉም ፡
የገጽ ብዛት ፡ 81
የታተመበት ዓመት ፡ 1996
ከመጽሐፉ ፡
ፆም አላህን የማምለክና ለትዕዛዙ የማደር ተምሳሌት ነው፡፡ ይህ ታዛዥነት የሰው ልጅ የአላህ አምላነት ዘወትራዊ እንደሆነና ሁልየም ከጎኑ መኖሩን እንዲያስታዉስ ይረዳዋል፡፡ ፆም የሰው ዘርን ለባርነት በዳረገው ማኅበራዊ ወግና ባህል እንዲሁም በራስ ስሜትና ፍላጎት ላይ ማመፅ ነው፡፡ ሰው ከፆም በፊት እንደሻው ይበላል፣ ይጠጣል ….
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: