የመጨረሻው ጉዞ

1.00 $

ይዘት ፡ መጽሐፉ መጠኑ አነስተኛ ቢሆንም በሚዳስሰው ርዕስ ዙሪያ በቂ እውቀት ከመያዙም በላይ ለየት ያለ አቀራረብ አለው። መጽሐፉ ያተኮረባቸው ሦስት ዋና ዋና አጀንዳዎች፥ የዱንያ ዓለም እውነታዎች፣ ወደ አላህ የሚደረገው ጉዞና ለምርመራው ቀን የሚደረገው ዝግጅትን በተመለከተ ቀላል ምሳሌዎችን በመስጠት ቀልብ የሚሞላ ትንተና ያደርጋል።

ይህን መጽሐፍ አጽንዖት ሰጥቶ በማንበብ በነዚህ ወሳኝ ጉዳዮች ዙሪያ ትክክለኛ ግንዛቤ ይዘን የተፈጥርንበትን ዓላማና መዳረሻችንን በመረዳት የጉዞ መስመራችንን ያስተካክልልናል፡፡

ዝግጅት : መጅዲ አል-ሂላሊ

ትርጉም ፡ ጁነይድ ዐብዱልመናን

የገጽ ብዛት ፡ 76

ከመጽሐፉ ፡

መቃብር መካከል ስንገኝ ይህች ዓለም ትክክለኛ የመኖሪያ ሀገር አለመሆኗ ሞትም ለማንኛውም ሰው የማይቀር ፅኑ የአላህ ውሳኔ መሆኑን እንረዳለን።

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ወ) እንዲህ ይላሉ፦ ቀብርን ዘይሩ፣ የመጨረሻዉም ዓለም ያስታውሳችኋልና፡፡ ሙታንን እጠቡ፤ ባዶ ቀፎ አካልን ማገላበጥ ጥልቅ ምክር ነውና፡፡ ጀናዛ ላይ ስገዱ፤ ምናልባት እንድታዝን ያደርግህ ይሆናልና፡፡ ያዘነ ሰው የትንሳኤ ቀን አላህ ጥላ ስር ነው።” (ሓኪም ዘግበውታል)

በየጊዜው ወደ መቃብር እየሄድን የዚያ ሥፍራ ነዋሪዎች ወደ ዱንያ ተመልሰው ያለፏቸውን ነገር ለማስተካከል፣ ያላቸውን ምኞት ማሰብ ይኖርብናል፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፦ “አጠር ያሉ የምትንቋቸው ወይም የምትጨምሯቸው ሁለት ረከዓ ሰላቶች -ወደ ሆነ ቀብር እያመለከቱ- ይህ ከሥራው ጋር ቢጨምራቸው ከዱንያችሁ ሁሉ ለሱ በላጭ ነው። (አልባኒ፣ ሲልሲለቱ ሰሒሐ (ሐ. ቁጥር 1288)

ኢብኑል ጀውዚ እንዲህ ይላሉ :- “ወንድሜ ሆይ! ከሞትክ በኋላ የሚኖርህን ሁኔታ ለማወቅ ከፈለግክ እስኪ ወደ ቀብር ሂድና ተመልከት፡፡ ቀብርህን በመቃብሮች መካከል አድርገህ ቁጠረው፡፡ ከዚያም በቀብርህ ዉስጥ ምን እንደሚያስፈልግህ አስብ፡፡ በዉስጡ ረጅም ጊዜ ስለምትቆይ ደግ ሥራዎችን አብዛ፡፡ ከዚህ ውጭ ያለው ነገር ቀብርህ ውስጥ ፀፀት እና ቁጭት ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ አሁን ያለህበትን ሁኔታ አስተውል፤ ለሞትና ለቀብር የሚጠቅም ከሆነ ቀጥልበት፤ ለነዚህ ለሁለቱ የማይጠቅም ከሆነ ግን ወደ አላህ ተመልሰህ የሚጠቅምህን ነገር ሥራ።” (ቡስታኑል ዋዒዚን)

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: