የመንገደኞች ስንቅ

1.00 $

ኢስላም አጠቃላይ የሆነ የሕይወት መርህ ነው፡፡ በዘፈቀደ የሚኖሩት ሃይማት አይደለም፡፡ ለብዙ ነገሮች ሥርዓት አድርጓል፡፡ አንዱ የጉዞ ሥርዓት ነው፡፡ በጉዞ ጊዜ የሚደረጉ ዚክሮች እና ዱዓዎች አሉ፡፡ ይህች አነስተኛ መጽሐፍ አንድ መንገደኛ ጉዞ ለማድረግ ካሰበበትና ቤተሰቡን ከሚሰናበትበት ጊዜ ጀምሮ ወደቤቱ እስኪመለስ ድረስ ሊከተላቸው የሚገቡ ሥርኣቶች፣ ሊያደርጋቸው የሚገቡ ዚክሮችና ዱዓዎች የተካተቱባት ነች፡፡
አዘጋጅ ፡ ኡስታዝ ያሲን ኑሩ
የገጽ ብዛት ፡ 95
የታተመበት ዓመት ፡ 1999
ከመጽሐፉ ፡ ማንኛዉም ሙስሊም በተለይ መንገደኛ ሰው ጉዞ ከመጀመሩ በፊት የበደለው ካለ ይቅር ሊባባል፣ የተበደረው ካለ ዕዳዉን ሊከፍል፣ ካሰበበት የጉዞ ቦታ ደርሶ እስኪመለስ ድረስ የሚበቃቸዉን ወጪ ሊያኖርላቸው ይገባል፡፡ መንገደኛ ጉዞዉን ከመጀመሩ በፊት ጓደኞቹንና ቤተሰቦቹን ዱዓ በማድረግ ሊሰናበታቸው ይገባል “ ለአላህ እተዋችኋለሁ፤ ለሱ የተተወ አደራ አይጠፋምና፡፡” በማለት፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት