Weight | 105 g |
---|
የሒጃብ ጥፍጥና
$1.00
አምላካችን አላህ (ሱ.ወ.) ያዘዘን ነገር ሁሉ ጣፋጭ ነው፤ እርካታ አለው፡፡ ሒጃብ የአላህ ትዕዛዝ ነዉና ሲለብሱት ደስ ይላል፡፡ ከሱ ዉጭ መሆንና መኖር ለሙስሊም ሴት ሰቀቀን ነው፡፡ መጽሐፉ በሒጃብ ዙርያ ይዳስሳል፤ የተደነገገበትን ዓላማ፣ መስፈርቱን፣ አስፈላጊነቱን፣ ትሩፋቱንና ሌሎችንም፡፡ መጽሐፉ ስለ ሒጃብ የተሳሳቱ ግንዛቤዎችን ያጠራል፡፡ አንዳንድ ምክሮችም ተላልፈዉበታል፡፡
አዘጋጅ ፡ ሰፊያ ዘግሉል
ትርጉምአሕመድ ሑሴን (አቡ ቢላል)
የገጽ ብዛት ፡ 104
የታተመበት ዓመት ፡ ነሐሴ 2000
ከመጽሐፉ ፡ አማኝ የሆነች አንድ ሴት አላህ (ሱ.ወ) ጌታዋ በመሆኑ የተደሰተች፣ የኢስላም ኃይማኖትም የሕይወቷ መርህ እንዲሆን በእርካታ የፈቀደች፣ እንዲሁም መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ነቢይና መልዕክተኛ መሆናቸውን በሙሉ ልቧ የተቀበለች ከሆነ ትዕዛዙን በማክበር እይታዋን ከባዕድ ወንዶች ላይ ሆነ ብላ ማንሳትና በአጋጣሚ የምታያቸው እንኳን ቢሆን በፍጥነት ዓይኗን በመስበር ታዛዥነቷን ማሳየት እንዳለባት ነው። መለኮታዊው ሕግ በግልጽ የሚያዝዘው ሴቶች ያልተፈቀዱላቸውን ወንዶች አትኩረው ከመመልከት ዓይኖቻቸውን እንዲሰብሩ ነው። ይህ ድርጊታቸው ልቦናቸውን ከሚጠሉትና የቆሸሹ አስተሳሰቦች በመከላከል መንፈሳቸውን የፀዳ ይሆን ዘንድ ታላቅ እገዛ ያደርግላቸዋል።
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት