Weight | 203 g |
---|
![1602665188Yelaqe_sebeena](https://nejashibooks.com/wp-content/uploads/2021/01/1602665188Yelaqe_sebeena.jpg)
የላቀ ስብእና
6.00 $
መጽሐፉ የአንድን ሰው ሕይወት ሊለዉጡ የሚችሉ አርባ ያህል ምክሮችን ይዟል፡፡ አዘጋጁ ለዝግጅቱ የተለያዩ ዓለማዊና ኢስላማዊ ምንጮችን በማጣቀሻነት ተጠቅሟል፡፡ እያንዳንዱን ምክርም መሣጭ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ ያብራራል፡፡ ከልብ ካነበቡት በርግጥም ሊለዉጡ የሚችሉ ምክሮች ናቸው፡፡
ዝግጅት ፡ ሙሐመድ ዑመር አደም
የገጽ ብዛት ፡ 256
የታተመበት ዓመት ፡ መጋቢት 2012
ከመጽሐፉ ፡ በመጽሐፉ ዉስጥ ተካተው ማብራሪያ ከተሠጠባቸው ምክሮች መካከል ፡ የሞራል ከፍታ ይኑርህ፣ የዉሳኔ ሰው ሁን፣ ተዓምርን አትጠብቅ፣ አዕምሮህን ዘግተህ አትቀበል፣ ራስህን አስተምር፣ በመጀመርያ እይታ አትፍረድ፣ ማምለጫው እያለህ ጠቡን አታርዝመው፣ ወጣትነትህን ተጠቀምበት፣ በባለፈው አትታሰር፣ የዉይይት ልምድህን አዳብር፣ ወሰን አላፊ አትሁን፣ ለስሜትህ አትማረክ፣ ከጠባብ ግድግዳ ዉጣ፣ ቁጣህን ተቆጣጠር፣ ስግብግብ አትሁን፣ የህሊናህን ንፅህና ጠብቅ፣ ልዩነቶችን በጥበብ ያዝ፣ ሚስጢር ጠባቂ ሁን፣ ታመን፣ ቅናትህን በልክ ያዘው፣ ጓደኛ ምረጥ፣ የህሊናህን ምሪት ችላ አትበል፣ በማንም ላይ በደል አትፈጽም፣ የፈጣሪህን እዝነት ፈልግ ….
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት