የህሊና ዕረፍት ቁጥር ሦስት

3.00 $

በአጫጭር ዐረፍተነገር ከጠቢባን፣ ከቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች እና የኢማን ሰዎች አንደበት የሚፈልቁ ቁምነገሮች እምቅ ትርጉምና ምትሃታዊ መልዕክት አላቸው፡፡ ሳይታሰብም ለብዙዎቻችን ትልቅ ትምህርትን ሠጥተው ያልፋሉ፡፡ ኢማናችንንም ያድሳሉ፡፡ ይህ መጽሐፍ በአጫጭር መልዕክቶችና አባባሎች ትላልቅ ቁምነገሮችን የሚያስታውስና የሚያስተምር ነው፡፡
ዝግጅት ፡ ሙሐመድ ሰዒድ
የገጽ ብዛት ፡ 76
የታተመበት ዓመት ፡ ነሐሴ 2003
ከመጽሐፉ ፡
– ሣንለምንህ ሁሉን ነገር የሰጠሀን ጌታችን ሆይ ! በለመንህ ጊዜ ከችሮታህ አትከልክለን ። ፀጋህን አትያዝብን ።
– እየሸሸንህ የጠራሀን አምላካችን ሆይ ! በመጣንና ፊታችን ወዳንተ በዞርን ጊዜ ተቀበለን አትመልሠን ።
– በዚህች ዓለም ላይ ሣለን መጥፎ ወንጀሎቻችን ሁሉ እያየህ የሠተርከንና ያለፍከን ፈጣሪያችን ሆይ ! ነገም በአኺራ በጭንቁ ቀን አታጋልጠን ።
– እያጠፋን የታገስከን አምላካችን ሆይ! በታዘዝንህ ጊዜ ጥረታችንን መዝግብልን ሩጫችንን ፃፍልን ።

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: