የሁለት ዓለም ጀነት

4.00 $

ይህ መጽሐፍ ነገ ያኛዉን ጀነት ከማግኘትህ በፊት የምድር ላይ ሕይወትህን ጀነት አድርገህ ኑር የሚል መልዕክት አለው፡፡ በአላህ ተደሰት፣ ክፍፍሉን ዉደድ፣ በሲሳዩ አመስግን ይላል፡፡ በዚህ መልኩ እሱ የወደደልህን ከወደድክ፤ ክፍፍሉን ካመሰገንግና ደስተኛ ከሆንክ ዛሬ ደስተኛ ሆነህ ትኖራለህ፤ ነገ ደግሞ አላህ ብሎልህ ጀነት ከገባህ ደግሞ ሌላ ደስታ ይጠብቅሃል ማለት ነው፡፡ ዛሬን በደስታ ከኖርክ ነገም ደስታን ከተጎናፀፍን በሁለቱም ጀነት ዉስጥ ኖርክ ማለት ነው፡፡ ከዚህ አንጻርም በምድር ላይ እንዴት ደስተኛ ሆኖ መኖር አንደሚቻል፤ ቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች ደስተኛ ሆነው ስለኖሩበት ሚስጢር ይጠቁመናል፡፡
አዘጋጅ – ኻሊድ አቡ ሻዲ
ትርጉም – ሙሐመድ ሰዒድ
የገፅ ብዛት ፡ 168
የታተመበት ዓመት ፡ ሚያዚያ 2010
ከመጽሐፉ ፡
የትኛውም ትርፍ የአምልኮ ተግባር አላህ ዘንድ ዉዴታን የሚያስገኘው ሲዘወተርበት ነው፡፡ አንድ ሁለት ቀን አሊያም አንድና ሁለት ሳምንት እየሠራ መተው የለበትም፡፡ አንድ ባሪያ በሱንና ተግባራት ወደ አላህ ከመቃረብ አይወገድም አላህም አስኪወደው ድረስ፡፡ የሚወደው ሲዘወትርበት፣ ሲፀና እና በተከታታይ ሲፈፅም ነው፡፡ ካልፀኑ ዉዴታ አይገኝም፡፡ ፅናት ለአላህ ዉዴታ ያበቃል፡፡ ቀልብም እየበራ የሚሄደው ዘውታሪነቱ ከፍ ባለ ቁጥር ነው፡፡
አቡ ሱለይማን አድ-ዳራኒ በአምልኮ ተግባራት ላይ መዘውተር ቀልብን እንደሚያበራ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ –
‹ መዘውተር ምንዳ አለው፤ እኔ እና አንተ አንዲት ሌሊት ቆመን ሁለት ሌሊቶችን ልንተኛ እንችላለን፤ አንድ ቀን ፆመን ሁለት ቀናትን ልናፈጥር እንችላለን፡፡ በዚህ ዓይነት አካሄድ ቀልብ ልትበራ አትችልም፡፡›
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 168 g