ዝንቅ

3.00 $

ከቁርኣን፣ ከሐዲስና ከተለያዩ መረጃዎች የተሰበሰቡ ከ100 በላይ አጫጭር ግን ሰፊ ሃሳብ የያዙ ቁም ነገሮችን ያካተተ ነው ዝንቅ፡፡ አዝናኝና አስተማሪ መልዕክቶች የተካተተቱበት ነው፡፡ ፀሐፊው ተመሳሳይ ሥራዎችን ከዚህ ቀደም ያሳተሙ ሲሆን በዚህ ቅልብጭ ብለው በሰዎች አዕምሮ ሊቀሩ በሚችሉ ቁርኣናዊ ነቢያዊና የሶሓቦች ገጠመኝ ሥራቸው ለአንባቢያን መልካሙን ዘይደዋል፡፡ መጽሐፉን በማንበብዎ በርካታ ቁም ነገሮችን ያገኛሉ የሚል እምነት አለን፡፡
አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ሰዒድ
የገጽ ብዛት ፡ 76
የታተመበት ዓመት : ጥር 2003
ከመጽሐፉ ፡
* በነፍስህና በስሜትህ ተበልጠህ ለትናንሽም ሆነ ለትላልቅ ወንጀሎች በቀላሉ እጅ የሠጠህ ቀን ።
* መልካም ነገርን እያየህ ከመሥራት ስትሠንፍ መጥፎዉን ደግሞ መጥፎነቱን እያወቅክ ስትዳፈር ።
* ለሙዚቃ ለድራማና ለፊልም ዉስጥህ ሲነካ ለቁርኣን ልብህ ሲደነድን ።
* ለዱኒያና ለጥቅሞቿ ስትሮጥ እንቅልፍ ስታጣ ለአኺራህ ግድ የለሽ ስትሆን ።
* ባመለጠህ ሀጠኣት የመሥራት እድል ስትቆጭ በጎ ለመሥራት ወኔ ሲከዳህ ።
* ሰላትህ ትርጉም ስታጣብህ ሩኩዕና ሱጁድ ጎንበስ ቀና ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ብቻ ሲሆንብህ ።
* ከዒባዳህ ጥፍጥና ስታጣ በአምልኮ ተግባርህ እርካታን ከተነፈግክ ።
* ጊዜህን ባልረባ ነገር ስትጨርስ ኸይር ሣትጨምር ቀን አልፎ ቀን ከተተካ ።
* የተዉባ በር ሁሌም ክፍት ሆኖ ሣለ ለመግባት ድፍረት ስታጣ ።
* አጀልህን መቃረቡን ስታዉቅ በበቂ አለመሠነቅህን ስትረዳ ።

አዎን ያኔ በደንብ አልቅስ ።

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: