ዘካ

3.00 $

ዘካ በኢስላም ውስጥ ካለው ከፍ ካለ ቦታ አንፃር ኅብረተሰባችን ስለ ዘካ ያለው ግንዛቤ እጅግ አናሳ ነው ማለት እንችላለን፡፡ ትኩረትን እየተነፈጉ ካሉ የኢስላም ግዴታዎች መካከልም አንዱ ነው፡፡ ብዙዎች የዘካን ጉዳይ ዘርዘር ባለ መልኩ አያውቁም፡፡ ይህ አነስተኛ መጽሐፍ ሦስተኛው የእስልምና ማዕዘን ስለሆነው ዘካ ምንነት፣ ዓላማው እና የዘካ የአወጣጥ ስልት በዕውቅ ዑለሞች የተከተቡ መጽሐፍትን በዋቢነት በመጠቀም ይዘረዝራል፡፡
የገጽ ብዛት ፡ 60
የታተመበት ዓመት ፡ 2008
ከመጽሐፉ ፡
አላህ (ሱ.ወ.) በቁርኣኑ ውስጥ ከሰማኒያ ሦስት በላይ በሆኑ አንቀጾች ላይ ‹‹ሶላትን ስገዱ፣ ዘካንም ስጡ….›› በማለት ከሶላት ጋር አቆራኝቶ በተደጋጋሚ ስለ ዘካ አውስቷል፡፡ ድግግሞሹ የጉዳዩን ክብደት ያሳያል፡፡ በየዘመናቱ የተነሱ ዑለሞችም ለዘካ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በርካታ ድርሳናትን በመፃፍ አብራርተዋል፡፡ ዘካ የእስልምና ማዕዘን ከመሆኑም በላይ ለግለሰብም ሆነ ለማህበረሰብ ከሚሰጠው ፋይዳ አንፃር ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡ የዘካን ግዴታ ባለመወጣት በግለሰብም ሆነ በማህበረሰብ ላይ ሊከተል የሚችለውን ጥፋት በየጊዜው ማስታወስ ይገባል፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ አኺራ በሄዱ ጊዜ አንዳንድ የዐረብ ጎሳዎች ዘካን ከልክለው ነበር፡፡ ኸሊፋ አቡበክር (ረ.ዐ.) ዘካን ከሶላት ነጥለው እንደማያዩ በመግለጽ ከልካዮችን ተፋልመዋቸው በግድ እንዲሰጡ አድርገዋቸዋል፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 79 g