Weight | 82 g |
---|
ዘላለማዊ ሃይማኖት
2.00 $
አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሃይማኖት ኢስላም ነው፡፡ ኢስላም ሁለንተናዊ ሃይማኖት ነው፡፡ አጠቃላይ የሕይወት ገጽታዎችን ይመለከታል፡፡ ኢስላም ብዙዎች እንደሚያስቡት የመስጅድ ሃይማኖት ብቻ አይደለም፡፡ በዚህም ሆነ በወዲያኛውም ዓለም ደስታን ለሚሹ፣ ለልብ ምቾት፣ ለሕሊና ዕረፍትና ለአዕምሮ ሠላም እና ለአካል ደሕንነት የሚለግስ የሕይወት ጐዳና መሆኑን ይህ መጽሐፍ ዘርዝሮ ይነግረናል፡፡ በዚህ መጽሐፍ የተለያዩ ተመራማሪዎች፣ ዶክተሮች፣ ታዋቂ ሳይንቲስቶች እስልምናን እንዲቀበሉ ያደረጓቸውን ነገሮች በመግለጽ በሃይማኖቱ ውስጥ የተቀመጡ ሥነ-ምግባራትን እና ተግባራትን የተመለከቱ መረጃዎችን የያዘ ነው፡፡
አዘጋጅ ፡ አሕመድ አ.አፍሺ
ትርጉም ፡ ዐብዱረሕማን ሰዒድና አደም ሰልማን
የገጽ ብዛት ፡ 72
የታተመበት ዓመት ፡ መጋቢት 2004
ከመጽሐፉ ፡ የሰው ልጅ በጥቃቅን እና ዉስብስብ ደረጃዎች ዉስጥ አልፎ መፈጠር፣ የአላህን ሱ.ወ. ትልቅ ተዓምር እንዲሁም ደግሞ አምላክ የለም ብለው ለሚክዱትም ፈታኝ ሁኔታ ነው፡፡ ኢስላማዊ ቤተመንግሥት ድንቅ ግቢ ነው፡፡ እያንዳንዱ ነገር ያለ ዓላማ አልተፈጠረም፣ አልተሠራም፡፡ ሳይንስንም፣ ትምህርትንም፣ ፍልስፍናንም የያዘ ግቢ- ኢስላም፡፡ ከዚህም በላይ ኢስላም የራቀቀ፣ ወንድማማችነት ያለበት፣ እኩልነት የሰፈነበት፣ እና ፍትህም የነገሠበት ሃይማኖት ነው፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት