ዕለተ ጁምዓ

1.00 $

ጁሙዓ የቀናት ሁሉ አለቃ ነው፡፡ የሙስሊሞች የሳምንቱ ዒድ ነው፡፡ የተቀደሰችውን የጁመዓ ቀን ሙስሊሞች በምን መልኩ ሊያሳልፏት ይገባል? ፡፡ በነቢያዊ ሐዲሶችና በቀደምት ሰለፎች ጁሙዓን በሚመለከት የተቀመጡ የተወደዱ የአምልኮ ተግባራት ምን ምንድናቸው?  ጁመዓ ለሙስሊሞች ሁሉ ያለው ዒባዳዊ ፋይዳስ ምንድነው? በዚህ መጽሐፍ ዉስጥ ተተንትኖ ቀርቧል፡፡
አዘጋጅ ፡ አወል ኸድር
የገጽ ብዛት፡ 32
የታተመበት ዓመት፣
ከመጽሐፉ :
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ብለዋል፡-“ጁሙዓን አላህ ከሌሎች ሕዝቦች ጠብቆ ለሙስሊሞች አቆይቷል። አይዱዶች ቅዳሜን ክርስቲያኖች ደግሞ እሁድን ኃይማኖታዊ የእረፍት ቀኖቻቸው አድርገው ያዙ። አላህ እኛ ሙስሊሞችን ወደ በላጩ ቀን ጁሙዓ መራን። በቀናት ቅደም ተከተልም ጁሙዓ፣ ቅዳሜ፣ እሁድ፣ ስንል ጁሙዓ ከሁለቱ ቀድሞ ይመጣል። ምድር ላይ እንደሆነው ሁሉ በፍርድ ቀንም ሙስሊሞች ከአይሁድና ከክርስቲያኖች ቀድመው ወደ አላህ ፊት ይቀርባሉ። እኛ ሙስሊሞች በታሪክ ከእነዚህ ሁለት ኃይማኖቶች በኋላ ላይ ብንመጣም በፍርድ ቀን ከፍጡራን ሁሉ ቀድመን እንዳኛለን።”
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 19 g