ዓፊያ

5.00 $

ሕይወት እንዳለው ሁሉ ሞትም አለ፤ ጤና እንዳለው ሁሉ በሽታም አለ፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) አንድንም በሽታ አልላከም፤ መድሃኒት ያኖረለት ቢሆን እንጂ ፡፡ ሰዎች ግን መድኃኒቱን ሊደርሱበትም ላይደርሱበትም ይችላሉ፡፡ ከበሽታ ለመውጣት ህክምና መሠረት ነው፡፡ ይህ መጽፍ በዓይነቱ የመጀመርያ የሆነ ተፈጥሯዊዉን፣ ነቢያዊዉንና ዘመናዊዉን ሕክምና ባቀናጀ መልኩ ለተለያዩ በሽታዎችና የሰዉነት እክሎቻችን ከሰዉነት ቆዳ ጅምሮ እስ ዉስጥ ህመም ድረስ መላና መፍትሄ የሚጠቁም በሚገባ ተደራጅቶ የቀረበ አማራጭ ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡
አዘጋጅ ፡ ጀማል ዐሊ ሙሐመድ
ትርጉም ፡ ሙሐመድ ዐብደላ ዐሊ
የገጽ ብዛት፡ 168
የታተመበት ዓመት ፡ 2010
ከመጽሐፉ ፡ ማር በዉስጡ በበቂ ሁኔታ ከአሥራ አምስት በላይ የተለያዩ የስኳር ዓይነቶች፣ ቫይታሚኖች፣ ፕሮቲን፣ የተለያዩ ማዕድናት፣ በርካታ ኢንዛይሞች፣ ፀረ ተህዋሲያን፣ ሆርሞኖች፣ የተለያየ ማዕድናት፣ ፎሊክ አሲድ እና ሌሎችንም.. ያያዘ ነው፡፡
ጥቁር አዝሙድ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ እርድ፣ ድኝ፣ ሩማን፣ ለውዝ፣ አብሽ፣ ፖም፣ የወይራ ዘይት፣ ሙዝ፣ እንቁላል፣ ዝንጅብል፣ … እና ሌሎችም በርካታ አትክልት፣ ፍራፍሬዎች፣ ጥራጥሬዎችና ቀጠላ ቅጠል በሕክምናው ዓለም ዉስጥ ያላቸዉን ሚና በዚህ መጽፍ ዉስጥ እንቃኛለን፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: