ዒባዳት አል-ሙእሚን

5.00 $

ይህ መጽሐፉ አንድ ሙእሚን የግዴታም ሆነ ሌሎች በፈቃደኝነት የሚፈፀሙ የአምልኮ ተግባራትን በምን መልኩ በማረና ለራሱ ጥቅምን በሚያስገኙለት መልኩ መፈጸም እንዳለበትና እንደሚችል ይጠቁመናል፡፡ ግዴታዎች ለመወጣት ብቻ የምንፈጽማቸውን የአምልኮ ተግባራት ሳይሆኑ ትርጉማቸውና ዓላማቸው ምን እንደሆነ ያብራራልናል፡፡ አምላካችንን አላህን (ሱ.ወ.) ይበልጥ እንድናውቅም ዕድል ይሰጠናል፡፡ የረሳነውን ያስታውሰናል፡፡ ከተዘናጋንበትም ያነቃናል፡፡ በዋናነት የሚያጠነጥነው በሶላት፣ ሐጅ፣ ዚክር፣ ዱዓ፣ ቁርኣንና ፆም ዙርያ ነው፡፡
አዘጋጅ ፡ ዶ/ር ዐምር ኻሊድ
ትርጉም ፡ ሙሐመድ ሰዒድ
የገጽ ብዛት ፡ 210
የታተመበት ዓመት ፡ 2009
ከመጽሐፉ ፡
በቁርኣን ዉስጥ ‹ሶብር/ትእግስት የሚለው ቃል 114 ጊዜ ያህል የተጠቀሰ ሲሆን ከሱ የተገኘ አሊያም የተራበ ቃልም 114 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ረጁል/ ወንድ ልጅ/ 24 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን ኢምረአህ/ሴት ልጅ/ እንዲሁ 24 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ሸህር /ወር/ የሚለው ቃል 12 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን የውም /ቀን/ የሚለው ቃል ደግሞ 365 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ኢብሊስ የሚለው ቃል 11 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን ከርሱ መጥጠበቅ/ኢስቲዓዛ/ ደግሞ 11 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ዘካት የሚለው ቃል 32 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን በረካህ/ረድኤት/ የሚለው ቃልም 32 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ዐቅል/አዕምሮ/ የሚለው ቃል 49 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን ኑር/ብርሃን/ የሚለው ቃል እንዲሁ 49 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: