ዑመር ኢብኑ ዐብዱልዐዚዝ

4.00 $

በተለምዶ የምናውቃቸው ኸሊፋዎች አራት (አቡበክር፣ ዑመር፣ ዑሥማን እና ዐሊ) ናቸው፡፡ ግና እጅግ ፍትሃዊ ከመሆናቸው የተነሳ ዑመር ኢብን ዐብዱልዐዚዝ 5ኛው የሙስሊሞች ኸሊፋ እስከመባል የደረሱ ናቸው፡፡ የዑመር ኢብን ዐብዱልዓዚዝ ስብእና እና የመሪነት ዘመን፣ ከጥንት ጀምሮ ዛሬም ድረስ በሕግ፣ በአስተዳደር፣ በፖለቲካና በታሪክ ዙሪያ ጥናት ለሚያደርጉ ተመራማሪዎች ተፈላጊ የጥናት መስኮች ናቸው፡፡ ከእስልምና ሊቃውንት መካከል ልዩ ሥፍራ የተሰጣቸው እኚህ ሰው፣ በጣም ባጭር ጊዜ የኸሊፋነት ዘመናቸው፣ በእስላማዊው ማሕበረሠብ ውስጥ ባመጡት እጅግ ጥልቅና ዘመን ተሸጋሪ ለውጥ ምክንያት የበርታ ጸሐፊያንን ቀልብ ገዝተው ኖረዋል፡፡ በተለይም በዘመኑ ተንሰራፍቶ የነበረውን ግፍና በደል ያስወገዱበት ፖለቲካዊ ህይወታቸው፣ ሁል ጊዜ እንደ አዲስ የሚፈተሽና ማራኪ የጥናት መስክ ሆኖ ዘልቋል፡፡ መጽሐፉ ስለ ዑመር የሕይወት ታሪክ ከዉልድት እስከ ዕድገት ኸሊፋነትና ህልፈት ይዳስሳል፡፡
አዘጋጅ ፡ ዐብዱልከሪም ታጁ
የገጽ ብዛት ፡ 192
የታተመበት ዓመት ፡ 2007
ከመጽሐፉ ፡
ዑመር ዜጎች እንደ ማበጠሪያ ጥርስ እኩል መሆናቸውን በተግባር ለማረጋገጥ ይሠሩ ነበር፡፡ እርሳቸው ዘንድ አረቡ አረብ ካልሆነው፣ ነጩ ከጥቁሩ ብልጫ አልነበረውም፡፡ በሙስሊሙ ማህበረሠብ ውስጥ አንዱ ከሌላው ሊበልጥ የሚችለው በተቅዋ ብቻ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት አንዱ አካባቢ ከሌላው አካባቢ ተለይቶ እንዲታይ አይፈቅዱም ነበር፡፡ ኡስማን ኢብን ሰዕድ አል-ዓዘሪይ ዑመር ዘንድ ቀርቦ ለኢራቃዊያን የተለየ እይታ እንዲኖራቸው በሚያግባባ መልኩ ያናገራቸው ጊዜ “በሰዎች መካከል ልዩነት አትፍጠሩ፡፡” በማለት ነበር የመለሱለት፡፡

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: