ኺላፍ

5.00 $

በሀሳብ መለያየት የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው፡፡ ሰዎች እንደ ዕውቀት ደረጃቸው፣ እንደደረሣቸው መረጃና ግንዛቤ ልክ የተለያየ አቋም ሊይዙ ይችላል፡፡ ይህ የአቋም መለያየት ጤናማ ነው፡፡ የግጭት መንስኤ መሆን የለበትም፡፡ የልዩነት እሣት ማቀጣጠል፤ ተጨባጭ ሁኔታዎችን ሳያጤኑና ሳይመረምሩ የአላህ ባሪያዎችን ማንቋሸሽና መዝለፍ እንጂ ሌላ ተግባር የሌላቸው ሰዎች ስለሚያደርሱት ጥፋት ከሁሉም የሙስሊሙ ዓለማት ስሞታ ሳይደርሰኝ ውሎ አያውቅም ይላሉ የመጽሐፉ አዘጋጅ፡፡ ለዚህም ይህንን መጽሐፍ ያዘጋጁት፡፡ የልዩነቶችን መኖር እንደ ጥሩ ነገር ማየት መልካም ነው፡፡ በመጽሐፉ ዉስጥ የልዩነቶች መንስኤዎችና መፍትሔዎቹ ሰፍረዋል፡፡
ዝግጅት ፡ ፕ/ር ኢማም ዩሱፍ አልቀርዷዊ
ትርጉም ፡ አምባሳደር ኡስታዝ ሐሰን ታጁ
የገጽ ብዛት ፡ 228
ከመጽሐፉ ፡ በእውነቱ ከሆነ የአስተሳሰብ ልዩነት (ኺላፍ) በራሱ አደጋ አይደለም። በተለይም በቅርንጫፍና እጅግም መሠረታዊ ባልሆኑ አጀንዳዎች ላይ የተለያየ እይታ መኖሩ ክፋት የለውም። አደጋው አላህ (ሱ.ወ)ና መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ያስጠነቀቁት በጠላትነት የመለያየት ስሜት ሲዳብር ነው። ይህም በመሆኑ በዳዕዋ ተግባር ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችም ሆኑ ስብስቦች (ጀማዓዎች)፡- ‹‹ ልዩነትን የማስተናገድ ጥበብ›› (ፊቅሁል ኢኸቲላፍ)ን መረዳት ያስፈልጋቸዋል።
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 208 g