ኸዋሪጅ እና ሺዓ

2.00 $

የመጽሐፉ ርዕስ፡ ኸዋሪጅ እና ሺዓ
መነሻ ሐሳብ፡ ዶ/ር ዐሊ ሙሐመድ አስ-ሶላቢ
ትርጉም፡ ሙሐመድ ሰዒድ
የገጽ ብዛት፡144
በእስልምና መንገድ ውስጥ ከተፈጠሩ ብዙ ቡድኖች ውስጥ ኸዋሪጅና ሺዓ ዋነኞቹ ቡድኖች ናቸው፡፡ በውስጣቸው የተለያዩ አይነቶች ሲሆኑ የተነሱበት መነሻ እሳቤዎችንም ይዘዋል፡፡ በዚህ መጽሐፍ የሁለቱን ቡድኖች ምንነት መጠነኛ ቅኝትና ዳሰሳ ያደርጋል፡፡ ኸዋሪጆች ከመልእክተኛው (ሰዐወ) ባልደረቦች ዘመን ጀምሮ እስካለንበት ጊዜ ድረስ አጥፊ እንደሆነና ለብዙ ጥፋቶች መነሻ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዋናነት ይህ ቡድን ራሱን የብቸኛ የእስልምና ጠበቃ አድርጎ የመመልከት ባሕሪያትም አዳብሮ ይገኛል፡፡ በዘመናችንም በተለያየ ሁኔታ ራሱን በመለዋወጥ ሰዎች ዘንድ ተሰራጭቶ ይገኛል፡፡ ሌላኛው በመጽሐፉ ስለተጠቀሰው የሺዓ ቡድን ደግሞ አይነትና አስተሳሰቡም ከተለያዩ የተገኙ ማጣቀሻዎችን በመጠቀም ስለምንነቱ ይገለጽበታል፡፡ መጽሐፉም ሰዎች እነዚህን ቡድኖች በዕውቀት በተደገፈ ሁኔታ እንዲያውቁትና በየጊዜው ከሚፈጠሩ ጽንፎችና አላዋቂነት እራሳቸውን እንዲከላከሉ ይጠቁማል፡፡

Category: