ኸሊፋ ዑሥማን (ረ.ዐ.)

2.00 $

የኢስላም ገናናነት ከሁለተኛው የሙስሊሞች ኸሊፋ ዑመር (ረ.ዐ) ሕልፈት በኋላም ቀጥሏል፡፡ ግና ከሦስተኛው ኸሊፋ ከዑሥማን ኢብን ዐፋን (ረ.ዐ) የኸሊፋነት ዘመን ማክተሚያ ጀምሮ የሙዓዊያ (ረ.ዐ) የበላይነት እስከ ተረጋገጠበት ጊዜ ድረስ (ከ36-60 ዓ.ሂ) የእርስ በርስ ግጭት ሰፍኖ ነበር፡፡ ይህ የዑሥማን ኢብኑ ዐፋን ታሪክ እነዚህንና ሌሎች የኸሊፋውን ከኢስላም በፊትና በኋላ፣ የሐበሻ ሀገር ስደት፣ ድሎቻቸው፣ የኢራቅ፣ ኢራን፣ አስተዳደርና ሌሎችም የኸሊፋውን ኢስላማዊ ተግባር ይተነትናል፡፡
አዘጋጅ ፡ ዶ/ር መጂድ ዓሊካን
የገጽ ብዛት ፡ 48
የታተመበት ዓመት ፡ ጥር 1987
ከመጽሐፉ ፡ ሐድረት ዑመር ከመሞታቸው ቀደም ብሎ ሙስሊሞች ከመካከላቸው ኸሊፋ እንዲመርጡና አዲስ ለተመረጠው ኸሊፋም ቃኪዳን ይገቡ ዘንድ ስድስት ትላላቅና የተከበሩ ሶሐቦች ያሉበት አንድ ኮሚቴ አቋቋሙ፡፡ ኮሚቴው ለረጅም ሰዓታት ስብሰባ ላይ ቢቀመጥም ከአንድ ዉሳኔ ላይ ለመድረስ ተሳነው፡፡ በዚህ ጊዜ ዐብዱረሕማን ኢብኑ ዐውፍ አንድ ሰው ራሱን ከምርጫው እንዲያገልና በጉዳዩ ላይ ከዉሳ ለመድረስ እንዲቻል ሀሳብ አቀረቡ …
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 54 g