ኸሊፋ ዑመር (ረ.ዐ.)

$2.00

ከአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ህልፈት በኋላ ሁለተኛው የሙስሊሞች ኸሊፋ የነበሩት ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ታሪክ የተካተተበት አነስተኛ መጽሐፍ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ቀለል ባለ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን የኸሊፋውን የሥልጣን ዘመን ከ13 እስከ 23 ዓ.ሂ ወይም እ.ኤ.አ 634-643 የኸሊፋውን ከልደት እስከ ኢስላምን መቀበል ያሳለፉትን ሕይወት፣ ኸሊፋው ለኢስላም ያበረከቱት ታላቅ አስተዋጽኦ፣ በጦርነቶች ያገኟቸው ታላላቅ ድሎች፣ የከፈቷቸው አገሮች… እና ሌሎችም ይተርካል፡፡

አዘጋጅ ፡ ዶ/ር መጂድ ዓሊካን
ትርጉም ፡ ዐሊ ሙሐመድ
የገጽ ብዛት ፡ 56
የታተመበት ዓመት ፡ መስከረም 1994
ከመጽሐፉ ፡ ኢስላም ተልዕኮዉን በጀመረ በስድስተኛው ዓመት ቁረይሾች ጉባኤ ተቀምጠው ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ.) የሚገድልላቸው ሰው ሲያፈላልጉ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ፈቃደኝነታቸዉን ገለፁ፡፡ ተሰብሳቢዎች ግድያዉን ለመፈፀም ሙሉ ብቃት ያለው ሰው እሱ ብቻ እንደሆነ በሙሉ ድምፅ ተስማሙ፡፡ ዑመር ሰይፋቸዉን መዘው ነቢዩን ፍለጋ ሲነጉዱ መንገድ ላይ ሰዕድ ኢብኑ አቢ ወቃስን አገኙ …
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: