ኸሊፋው አቡበክር (ረ.ዐ.)

2.00 $

ከአላህ መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ. ህልፈት በኋላ የመጀመርያው የሙስሊሞች ኸሊፋ ሆነው የተመረጡ ናቸው፡፡ “አስ-ስዲቅ” /እውነተኛው/ በመባል የሚታወቁ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ወዳጅ ናቸው፡፡ በአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ያመኑ የመጀመርያ ሰዉም ናቸው፡፡ ይህች አነስተኛ መጽሐፍ ስለርሣቸው ማንነትና የሕይወት ታሪካቸው ታስቃኘናለች፡፡
አዘጋጅ ፡ ዶ/ር መጅዲ ዐሊ ካን
ትርጉም ፡ ዐሊ ሙሐመድ
የገጽ ብዛት ፡48
የታተመበት ዓመት ፡ መስከረም 1994
ከመጽሐፉ ፡ አቡበክር አስስዲቅ በቅድስቲቱ የመካ ከተማ በ573 ዓ.ል ነው የተወለዱት፡፡ በ571 ከተለወለዱት ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) በሁለት ዓመት ያንሳሉ፡፡ የአባታቸው ሥም ዑሥማን ሲሆን እናታቸው ሰልማ ይባላሉ፡፡ አባታቸው አቡ ቁሓፋ፤ እናታቸው ኡሙል ኸይር በመባል ይታወቃሉ፡፡ ከልጅነታቸው ጀምሮ በእርጋታ ነበር የሚታወቁት፡፡…
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: