Weight | 73 g |
---|
Hadith
ኩኑዝ
1.00 $
ነብያዊ ሐዲሦች አይጠገቡም፡፡ ጣፋጭ እነ የሥጋም የመንፈስም ልዩ ምግቦች ናቸው፡፡ ነብያችን (ሰ.ዐ.ወ.) ንግግራቸው ትልቅ ትምህርት አለው፡፡ ጥበባዊ ንግግራቸውጥልቀትና ምጥቀቱ ከሌሎች የሰው ልጅ ንግግሮች ከፍ ያለ ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ዉስጥ በተለየ መልኩ እና በአስደናቂ ሁኔታ ትንተናና ማብራሪያ የተሠጠባቸው የተመረጡ ሐዲሦች ተካተዋል፡፡
አዘጋጅ ፡ ናዲያ ሐሰን
የገጽ ብዛት ፡ 67
የታተመበት ዓመት ፡ 1988
ከመጽሐፉ ፡
አንደኛ ሐዲሥ ፡ ከእናንተ አንዳችሁ በእጁ የተምር ችግኝ እንደያዘ ቂያማ ቢደርስ ለመትከል ዕድል እስካገኘ ድረስ ይትካላት፡፡ በዚህች ምግባሩ አጅር ያገኝበታልና፡፡”
ይትካላት ! ምኗን ከዓመታት በኋላ ካልሆና የማታፈራ የተምር ችግኝ፡፡ ከሰኮችዶች በኋላ ቂያማ ሊቆም! ዓለም ልትጠፋ! ምድር እንዳልነበረች ልትሆን! … በዚህ ሁሉ መሃል ይተከላት ይላሉ የአላህ ነቢይ፡፡ ምንኛ እፁብ ድንቅ አስተምህሮ ነው!!
ኢስላም ለዚህም ሆነ ለዚያኛው ዓለም ትልቅ ግምት ይሠጣል፡፡ ሰዎች የሁለቱንም ዓለም ድርሻ እንዲወጡ ይመክራል፡፡ አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ መሄድን አይደግፍም፡፡
አሳታሚ ነጃሺ ማተሚያ ቤት