ከኢማን አድማስ

2.00 $

ይህ መጽሐፍ ሁለት ክፍሎች ሲኖሩት የመጀመሪያው ክፍል የእምነትን አስፈላጊነት ይተነትናል፡፡ በዚህም የሰውን ልጅ ከየት መጤነቱን? ለምን ዓላማ መፈጠሩንና ወደየት እንደሚሄድ በሦስተኛ መደብ የአተራረክ ዘዴ ጠይቆ ይመልሳል፡፡ በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የሰው ልጅ ሊያስተውልና ሊያስተነትን እንደሚገባ መክሮ ተፈጥሮን ፍጡራንን በተለይም የሰውን ልጅ ሁለንተና እንድናጤን ከቁርኣንና ከሐዲስ እየጠቀሰ ያስተምራል፡፡

አዘጋጅ ፡ ሸይኽ አብዱልመጂድ አዘንዳኒ
ትርጉም ፡ ናዲያ ሐሰን
የገጽ ብዛት ፡ 72
የታተመበት ዓመት ፡ ሐምሌ 1987
ከመጽሐፉ ፡ የማን ንብረት ነን ?.. ይህች የምትመገብባት እጅህ፣ የምትናገርባት ምላስህ፣ የምትጓዝባት እግርህ፣ የምታስብበት አዕምሮህ፣ አጠቃላይ ቁሳዊ ሀብትህም ሆነ መላው አንተነትህ፣ የምትገለገልባቸው ነገሮች ሁሉ የማን ናቸው? አንተ ማነህ? የማን ሀብትና ንብረት ነህ? ወደዚህች ዓለም የመጣኻው በምርጫህ ነውን ? ማነው ከምንም ያስገኘህ? ከእርከን ወደ እርከን ያሸጋገረህ ?…
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: