ከአላህ ጋር

3.00 $

ይዘት ፡ መጽሐፉ በአጠቃላይ ሀሳቡ ከአላህ ጋር የመሆንን አስፈላጊነት ያወሳል። ከአላህ ጋር ሲሆኑ የተመኙት ሁሉ እንደሚሳካ፣ ምድራዊ ደስታም ሆነ አኺራዊ ስኬት እንደሚገኝ ይገልፃል። ከአላህ ጋር መሆን ሲባል ሁሌ እሱን በማሰብ በሃሳብ ሊሆን ይችላል፣ እሱን በማውሳትና በማወደስ ሊሆን ይችላል፣ እሱን በሁሉም ነገር ውስጥ በማስገባት ሊሆን ይችላል፣ በቃልም ሆነ በተግባር አላህን በማስታወስ ሊሆን ይችላል፣ በአምልኮ ተግባራት በመበርታት ሊሆን ይችላል … ሌላም ሌላ።

መጽሐፉ ከአላህ ጋር የተኖሩ የሕይወት ተሞክሮዎችን በማነሳሳት ከአላህ ጋር መኖር ለሕይወታችን ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የሚያስታውስ ነው።

አዘጋጁ በመጽሐፉ ዉስጥ ከሁሉ ነገር ውስጥ ከአላህ ጋር የመሆንን ፋይዳን ይሰብካል፤ ያመላክታል፣ ይጠቁማል። አስተዋሽ ሲጠፋ፣ ሃሳብ ሲገባን፣ ሲደብረን፣ ስልችት ሲለን፣ ሲጨንቀን፣ ስንባክን… ይህን መጽሐፍ እንድናነሳም ይመክራል።

አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ሰዒድ

የገጽ ብዛት ፡ 152

የታተመበት ዓመት ፡ ታህሳስ 2013

ከመጽሐፉ ፡

ኸልዋ ለዚክር፣ ለዒባዳ እና ተገልሎ ወደ አላህ (ሱ.ወ.) ለማልቀስ ብቻ አይደለም አስፈላጊነቱ፡፡ በዱንያ ሩጫዎች መሃል ቆሞ ብሎ ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅና ራስን ለመገምገም፤ ከግምገማ በኋላም ጥሩ ዉጤት ይዞ ለመውጣት ኸልዋ አስፈላጊ ነው፡፡

ከአላህ ጋር ተገልለው ለብቻ ሲሆኑ ኸልዋ መደበቅ ሳይሆን ጎልቶ መታየት ነው፡፡ መጥፋት ሳይሆን መኖር ነው፡፡ ወደ አላህ መቅረብ ነው፡፡ ጌታዬ ሆይ እየኝ እዚህ ነኝ ማለት ነው፡፡ ለሃኪም እንደሚደረገዉና ሁሉ ነገር በግልጽ እንደሚነገረው፤ አልትራሳዉንድ ፊት በሽታን ለመፈተሸ እራቁት እንደሚቀረበው ሁሉ አላህ ፊት በመቅረብ ሁሉን ገላልጦ ማሳያ ቦታ ነው ኸልዋ፡፡

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: