Weight | 28 g |
---|
Hereafter
ከሞት በላይ ምን መካሪ አለ?
1.00 $
ሞት ሁሉም ፍጥረት የሚገባው በር ነው፡፡ ከሞት የሚቀር ማንም የለም፡፡ ሞትን ማስታወስ በዚህ ምድር ላይ ተዘናግተንና ተደላድለን እንዳንኖር፣ የመጨረሻዉን ዓለም እንዳንረሳ ይረዳናል፡፡ ከየትኛዉም ምክር በላይ ሞት መካሪና አስተማሪ ነው፡፡ ብልህ ማለት ነፍሱን የመረመረና ለመጪው ሕይወቱ በርትቶ የሠራ ነው፡፡ መጽሐፏ ሞት ለኛ ምን ያህል ቅርብ እንደሆነ ታስታውሰናለች፡፡ በሞት እንድንመከርም፤ ከሞት በኋላ ላለው ሕይወትም እንድንዘጋጅ ትጠቁመናለች፡፡
አዘጋጅ ፡ ዳር አል-ወጠን
ትርጉም ፡ አሕመድ ሑሴን (አቡ ቢላል)
የገጽ ብዛት ፡ 40
የታተመበት ዓመት ፡ ሕዳር 2005
ከመጽሐፉ ፡ ሞት የሕላዌ የመጨረሻ ደረጃ እንደሆነ የሚያስብና ከዚያ በኋላ መጥጠየቅ፣ ምርመራ፣ ጀነትና ጀሀነም የለም ብሎ የሚያስብ ሰው ሲበዛ የዋህና ተላላ ነው፡፡ ሁኔታው እዲህ ቀላል ቢሆን ኖሮ የሕይወትና የመፈጠር ግብ ከጀርባው ጥበብ የተጓደለዉና ሁሉ ነገር ትርጉም አልባ በሆነ ነበር፡፡ …
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት