እኛና ሶሐቦች – ልዩነቱ ሰፍቷል

2.00 $

መጽሐፉ የታዋቂዉን ዳዒ የሸይኽ ካሊድ አር-ራሺድን የተለያዩ የካሴት ሥራዎችና ሙሓደራዎች መሠረት አድርጎ የተሠራ ነው፡፡ መጽሐፉም አንድ ከፊት ለፊታችን ቆሞ የሚገስጸን ሰው የሚያደርጋቸው ንግግሮች የሚኖራቸውን መልክ የያዘ ነው፡፡ በውስጡም ሁለት የሚጓዙበት ጎዳና አቅጣጫው የተለያየ የሆኑ ሰዎችን ባህሪያት ይዘረዝራል፡፡ አብዛኛው ጽሑፉም ጥያቄያዊ እና ከውስጣችንም ጋር እንድንነጋገር መድረክ የሚከፍትልን ይሆናል፡፡ የትርጉም ሥራው “ልዩነቱ ሰፍቷል” ተባለው ከቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች አንፃር ምን ያህል ወደኋላ እንደቀረን ለማመላከት ነው፡፡ አላህ ይዘንልም፡፡
አዘጋጅ ፡ ሸይኽ ኻሊድ አር-ራሺድ
ትርጉም ፡ ጀማል ሙሐመድ
የገጽ ብዛት ፡ 56
የታተመበት ዓመት ፡ ማጋቢት 2008
ከመጽሐፉ ፡
ይህች መልዕክት ለነዚያ በኃጢያት ዋና ለደከሙ፣ ለነዚያ በወንጀል እና ከአላህ ቤት በመራቅ ምክንያት ፊታቸው ላይ የመጥፋት መንፈስ ለሚነበብባቸው ወንድሞች ናት፡፡ ይህች መልዕክት ለነዚያ በአላህ ላይ ድንበር በማለፋቸው ምክንያት ትልቁ የአላህ (ሱ.ወ) ፀጋ ከእነርሱ ላይ ተነስቶ የአላህ ቁጣ ለሰፈነችባቸው ናት፡፡ ይህን አሰመልክቶ ታላቁ ታቢዒን ሰዒድ ኢብን ሙሰየብ እንዲህ ይላሉ፡- “የአላህ ባሪያዎች ለአላህ ታዛዥ ከመሆን በላይ ለነፍሳቸው ክብር አያገኙም፣ ኃጢያት ከመፈፀም በላይ ነፍሳቸውን የሚያዋርዱበት መንገድ የለም፡፡”
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: