ኢትዮጵያ እና ኢስላም

3.00 $

የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የቅርብ ተከታዮችና ባልደረቦች (ሶሓባዎች) በእምነታቸው ምክንያት በደረሰባቸው ግፍ የተነሳ ወደ አገራችን ኢትዮጲያ ተሰደው ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ዘንድም ለ16 ዓመታት በመቆየታቸው በሕዝቡ እምነት ባሕልና የአኗኗር ዘይቤ ላይ ያደረሱት ተጽእኖ ቀላል አልነበረም፡፡ ይህ መጽሐፍ ኢትዮጲያ እና እስልምና ያሳለፉትን ታሪክ ይዳስሳል፡፡ የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ.) ተከታዮች ስደት ከነጃሺ አስሐማ ታሪክ ጋር በማቆራኘት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ይሰጣል፡፡

አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ጦይብ ኢብኑ ሙሐመድ
ትርጉም ፡ ዶ/ር ኢድሪስ ሙሐመድ
የገጽ ብዛት ፡ 112
የታተመበት ዓመት ፡ መጋቢት 1991
ከመጽሐፉ ፡ ኢትዮጲያ ከመካከለኛው ምሥራቅ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኝ በመሆኗ በዚሁ ክልል የሚከሠቱ ለውጦች እና ንቅናቄዎች ሳይዳስሷት አያልፉም፡፡ የመካከለኛው ምሥራቅ የሦስት የዓለማችን ታላላቅ ሃይማኖቶች (አይሁድ፣ ክርስትና እና እስልምና መፍለቂያ ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ በርካታ የአላህ ነቢያትም በዚሁ ክልል ተወልደው ከዚሁ አካባቢ በመላክ ለአላህ መልዕክተኛነት ማዕረግ በቅተዋል፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: